🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

። የኔ ብዬ ስዬሽ ሙሉ እድሜን ልኖር ካንቺ ጋር ስዳራ ላይሰሙኝ ጆሮዎችሽ ስምሽን ደጋግሜ በልቤ | ህብረ ቀለማት ግጥሞች


የኔ ብዬ ስዬሽ
ሙሉ እድሜን ልኖር ካንቺ ጋር ስዳራ
ላይሰሙኝ ጆሮዎችሽ
ስምሽን ደጋግሜ በልቤ ስጣራ
መስማት አትችል ይሆን
እያልኩኝ ቀን ተሌት ስፋጠጥ ስፈራ

ንግግሬ ታክቶሽ ሰማው ስታወሪ
ያላንዳች ምስክር ያላንዳች አባሪ

አንቺ ስታወሪ
ስውር ነው ድምጸትሽ
ረቂቅ ነው ቃልሽ
አንቺ ስታወሪ
አይኖቼ ይሰማሉ
የልቤ ምቶቿ አንቺን አምጣ ይላሉ

ግና
ምን ዋጋ አለው ታድያ
አንቺን ለማናገር ብሞክር በመላ
ሆነሽ ከተገኘሽ
ሳናግርሽ የኔ ስታወሪ የሌላ..
ምን ዋጋ አለው
እናት?
ምን ትርፍ አለው ማየት ጣትሽ ተሽቆጥቁጦ
የማውቀው ቀለበት ከጣትሽ አምልጦ
ምንስ ትርጉም አለው
ልብሽ ላያስበኝ ስሜን ሺ ቢጣራ
አይንሽ ቢፈልገኝ ቀን ሌት በጠራራ
ምኑ ሊገባኝ ነው ቅኔ ሆኖ ተግባርሽ
ስትፈልጊ ብቻ ሁል ጊዜ እማገኝሽ
ባል ልሁን ወንድምሽ??
አኒታ