🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ህብረ ቀለማት ግጥሞች

Logo of telegram channel ethiopiagna — ህብረ ቀለማት ግጥሞች
Logo of telegram channel ethiopiagna — ህብረ ቀለማት ግጥሞች
Channel address: @ethiopiagna
Categories: Uncategorized
Language: English
Subscribers: 1.64K
Description from channel

ህብረ ቀለማት ግጥሞች የተሰኘው ቻናላችን የተለያዩ በመድብል ደረጃ ለንባብ ያልበቁ ፝ የፍቅር ፝ የሀገር ፝ የነገር ፝ እና ሌሎች ሀገርኛ ጣዕመ ዜማ ያላቸውን ግጥሞች እምንለቅበት ሲሆን እናንተ ከየትኛው ጎራ እንደሆናቹ እራሳቹን እምፈትኑበት አንዳንድ ውድድሮች ይኖሩናል።
@lanchi_new11
@ethiopiagna
@ethiopiagna11
For daily poems @EthPoetrybot

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


The latest Messages 2

2021-04-21 06:44:58
1.6K views03:44
Open / Comment
2021-04-17 07:18:49 ሚስጥራዊ መልስ
.......................
ምን ነበር ካንገትሽ
ከደረትሽ ስቦ ውስጥሽ የሚከተኝ
ምንድን ነው ጠረንሽ
ሳልጠጋሽ ገና የሚያንከተክተኝ
ምን ናቸው እጣቶችሽ
በዳሰሳ ብቻ አለም የሚያስረሱ
ምን ናቸው እግሮችሽ
ገና ከሩቅ ሲያዩኝ ኖር ብለው እሚነሱ
ከናፍርሽሳ ምንድን ነው ጣዕሙ
ምንድን ነው ስሬቱ
አይን ሁሉ ነገርሽ ምን ይሆን ውበቱ
ምንድን ነው ሚስጥርሽ ፍቺሽ ከየት አለ
መልስ አገኝሽ ዘንዳ ባገባሽ ምንአለ...
#anita
1.7K views04:18
Open / Comment
2020-11-29 07:13:03 የሰው ልጅ ትክክለኛ ባህሪ ሲገለጥ!!

. አሪፍ ፀባይ አለዉ የምትለዉ ሰዉ ለብቻዉ ሲሆን ትክክለኛ ነገር ይሰራል?

• የካፌ አስተናጋጅ፣ ፅዳት የሚሰሩ ሰዎችን፣ ነዳጅ የሚቀዱ ሰዎችን እንዴት ነዉ የሚያነጋግራቸዉ?

• ሰዉ ገንዘቡንና ሰአቱን የሚጠቀምበት መንገድ የሰዉየዉን ስብእና በትክክል ይናገራል፡፡

አባቴ ሳምንቱን ሙሉ በስራ ተወጥሮ ነዉ የሚያሳልፈዉ፡፡ እቤት ሲመጣ እንኳን አመሻሽቶ፣ ከስራ ደክሞት ነበር፡፡

ማታ የቀረዉን ትንሽ ሰአት ለኛ 'እንደአባት' ለእናታችን ደግሞ 'እንደባል' የሚገባዉን ሁሉ ይረዳን፣ ያግዘን ነበር፡፡

በሱ እድሜ ያሉ ብዙ ሰዎች ልክ እቤት ሲገቡ ቲቪ ላይ ተጥደዉ እንደሚያመሹት ሳይሆን እኛን የቤት ስራ በማገዝ፣ እናቴን ደግሞ ከጎኗ ሆኖ ጅርባዋን ሲያሽ፣ እግሬን ቆረጠመኝ ስትለዉ እግሯን ቁጭ ብሎ በቫዝሊን ሲያስታምም ነበር ልጅነቴን የማስታዉሰዉ፡፡

እንደአባቴ አይነት 'የገባበትን ሃላፊነት በትክክል አዉቆ' ቤተሰቡን ብር ከመወርወር ባለፈ ተንከባክቦና ደግፎ አሳድጎናል፡፡

ለዚህ ነዉ መልካም የሆኑትን እንቁላሎች ከተበላሹት ለመለየት ዉሃ ዉስጥ የሚከተተዉ፡፡

የችግርና የመከራ ወቅት ሲጀመር የምትወደዉ ሰዉ ማንነት በትክክል እየጠራ፣ እየታየና እየተገለጠ ይመጣል፡፡

ሰናይ ቀን!

@Ethiopiagna
3.2K views mïçkéŷ, 04:13
Open / Comment
2020-11-28 06:00:02 "ቀንህን በጎ ሀሳቦችን በማሰብ ጀምር"

ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነቃ ምስጋና በማቅረብና ስለ ቀኑ መልካምነት ለራስህ በመንገር ፋንታ "ኤጭ ዛሬ ቀኑ እንዴት ይቀፋል?አሁን እንዴት ብዬ ነው ወደ ጉዳዬ የምሔደው?!" ብትል ወይ ከስራህ አልያም ከትምህርትህ ወይም በአጠቃላይ ከምትሔድበት ትቀራለህ ወይ ታረፍዳለህ።ከሔድክም በፍላጎት አትሔድም። በማርፈድህ ወይ አለቃህ ወይም መምህርህ ሊናደድብህና ሊቆጣህ ይችላል።

ለጉዳዩ የሚኖርህን ፍላጎት በጠዋት የምትይዘው መጥፎ ስሜት ይሰርቀዋል። ይህን ስሜት የሚወልደው ደግሞ የገዛ ሀሳብህ ነው። መሳሳብ ማለትም ይኸው ነው። ሀሳብህ አቻ ስሜታዊ ይዞታን ሲያስከትልብህ ስሜትህ ደግሞ በተራው እውነታህን ይፈጥራል።

በእርግጥ ስሜታዊ ይዞታህ ሙሉ በሙሉ በጥዋቱ ሀሳብህ ላይ የሚመረኮዝ አይደለም። በተወሰነ መልኩም ቢሆን ማታ ወደ መኝታህ ስታመራ ይዘህ የነበረው ሀሳብ ላይም ጥገኛ ሊሆን ይችላል። የማታው ሀሳብህ የቀኑ ውሎህን ሲመስል፤ የቀኑ ውሎህ ደግሞ በበፊተኛው ጠዋት ደጋግመህ ያሰብከው ሀሳብህ ማለት ነው።

መልካም ቀን!

@Ethiopiagna
2.5K views mïçkéŷ, 03:00
Open / Comment
2020-11-27 06:00:02 እኛም ባለጠጎች ነን!

በአለም ላይ ብዙ ሰዎች ባለጠጋ ሆነው ሳለ ራሳቸውን ድኃ እንደሆኑ በማሳመን ከእምቅ ብቃታቸው በታች ኖረው ያልፋሉ፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት ባለጠጋ የሚለውን ቃልና ሃሳብ በሚገባ ስለማይገነዘቡት ነው፡፡ አንዳንዱ የሕብረተሰብ ክፍል “ብልጽግና” ለሚለው ቃል የሰጠንን ትርጉም ተቀብለው ያንን ሲጠባበቁ በእጃቸውና በውስጣቸው ያላቸውን ሃብት ሳይጠቀሙ ያልፋሉ፡፡

ብልጽግና ሁለንተናዊ ነው፡፡ ብልጽግና ገንዘብን ብቻ ሳይሆን ማንነትና ራእይን ያካተተ ነው፡፡ አየህ፣ ሰው ብዙ ገንዘብ ኖሮት ስግብግብ ከሆነ ብልጽግናው ምኑ ላይ ነው? ሰው ባለስልጣን ሆኖ ጨካን ከሆነ ብልጽግናው የቱ ጋር ነው? ሰው አዋቂ ሆኖ ትእቢተኛ ከሆነ የበለጸገው በምንድነው? ሰው ባለሞያ ሆኖ በዝባዥና ሌባ ከሆነ በለጸገ የሚባለው እንዴት ነው? እነዚህ ሁሉ የድህነት እንጂ የብልጽግና ምልክቶች አይደሉም፡፡

ሃብትና ብልጽግና አንጻራዊ ነው፤ እንዲሁም ሁለንተናዊ ነው፡፡ ስለዚህም፣ የሕይወትህን ዓላማ ካወቀክና ይህ ዓላማህ ለህብረተሰቡ አንድን መፍትሄ የሚያመጣ ከሆነ አንተም ባለጠጋ ነህ! ለለየኸው ዓላማህ የሚመጥን ፈቃደኝነትና ትጋት ካለህና ያንን ለማዳበር በመንቀሳቀስ ላይ ከሆንክ አንተም ባለጸጋ ነህ!

ዓላማህን በመከታተል ጉዞህ ደስተኛ ከሆንክና በዙሪያህ ለሚገኙ ሰዎች የደስታና የመነሳሳት ምንጭ ከሆነክ አንተም ባለጠጋ ነህ!
ዶ/ር እዮብ ማሞ

ሰናይ ቀን!

@Ethiopiagna
2.2K views mïçkéŷ, 03:00
Open / Comment
2020-11-26 06:00:02 በጊዜያዊ ስሜቶች (“ሙዶችህ”) አትታለል

ሰው በተፈጥሮው መልካም ገጠመኝ ሲደርስለትና በጣም በጋለና ግሩም በሆነ ስሜት (“ሙድ”) ውስጥ ሲሆን ከዚያ ቀን ጀምሮ ልብህን የሚያሳዝን ምንም ነገር እንማይገጥመው የማሰብ ዝንባሌ አለው፡፡ በተቃራኒውም በአንዳንድ ክፉ ገጠመኞች ምክንያት በጣም በወደቀ “ሙድ” ስሜት ውስጥ ራሳችንን ስናገኘው ከዚያ ሁኔታ የመውጫ ጭላንጭሉ አይታየንም፡፡ ይህ ከጊዜው “ሙድ” የተነሳ የሚመጣ “የቋሚነት” ስሜት በውሳኔአችን ላይ ጣልቃ ይገባና የኋላ ኋላ የምንጸጸትባቸውን ውሳኔዎች እንድንወስን ይገፋፉናል፡፡

ለምሳሌ፣ ይከፈለትልኛል ብለህ የጠበከው የእድል በር ባልጠበከው መንገድ ቢዘጋና የወደቀ “ሙድ” ውስጥ ብትሆን፣ ኑሮ ሊያስጠላህና የተለያዩ ውሳኔዎችን እንድትወስን ሊገፋፋህ ይችላል፡፡ “ሙዱን” ግን ማሳለፍ የግድ ነው፡፡ አየህ፣ በክፉም ሆነ በጥሩ የጠለቀ ስሜት ውስጥ ስትሆን አእምሮህ ለሕይወትህ የሚጠቅምህንና የማይጠቅምህን ነገር የማመዛዘኑ ሁኔታ ይወርዳል፡፡ እነዚህ የ“ሙድ” ውጣውረዶች ግን እየመጡ የሚሄዱ እንደሆኑና፣ እውነታ ብቻ ዘላቂ እንደሆነ በማሰብ አይኖችህን እውነታው ላይ ጣል - የማያልፍ ነገር የለምና።

ሠናይ ቀን!

@Ethiopiagna
1.9K views mïçkéŷ, 03:00
Open / Comment
2020-11-25 06:00:03 ቅደም ተከተልን የማወቅ ጥበብ

“የሚያጣድፍ ነገር ሁሉ አስፈላጊ ነገር አይደለም” - Stephen Covey

አንድ ቀን አንድ የማኔጅመንት ሳይንስ ሊቅ ለተማሪዎቹ ንግግር በማድረግ ላይ ነበር፡፡ ይህ ሰው ለእነዚህ በጣም ለተነሳሱና ብሩህ አእምሮ ላላቸው ተማሪዎች በመናገር ላይ እያለ አንድን ነገር አደረገ፡፡ አንድ ባሊ አመጣና ጠረጴዛው ላይ ካስቀመጠ በኋላ ድንጋዮችን በማምጣት ባሊውን አፉ ድረስ ጢም አድርጎ በድንጋይ ሞላው፡፡ ይህንን ካደረገ በኋላ፣ “ይህ ባሊ ሙሉ ነው የሚል እጁን ያውጣ” አለ፡፡

በክፍሉ ያሉ ተማሪዎች በሙሉ እጃቸውን አወጡ፡፡ “እርግጠኛ ናችሁ?” አላቸው፡፡ “አዎን” በማለት እርግጠኝነታቸውን አረጋገጡለት፡፡ ከዚያም ከጠረጴዛው ስር አስቀምጦት ወደነበረው ሌላ ባሊ አጁን ዘርግቶ አነሳውና በውስጡ ያለውን ጠጠር ወደዚያ ድንጋይ ሞልቶበት ወደነበረው ባሊ አፈሰሰው፡፡ ጠጠሮቹ ሹልክልክ እያሉ ባገኙት ቀዳዳ ሁሉ ገቡ፡፡

“አሁንስ ባሊው ሙሉ ነው የምትሉ ስንት ናችሁ?” አለ መልሶ፡፡ አሁን አሰልጣኙ ምን ሊል እንደፈለገ በመጠኑ እየገባቸው ስለመጣ በማንገራገር የተደባለቀ ምላሽ ሰጡት፡፡ አንዳንዶቹ፣ “አሁን ሙሉ ነው” ሲሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ፣ “አሁንም አልሞላም” አሉ፡፡ አሁንም በመቀጠል እጁን ወደ ጠረጴዛው ስር ሰደድ በማድረግ ሌላ ባሊ አነሳ፡፡
ይህኛው ባሊ በአሸዋ የተሞላ ነው፡፡ ወዲያውኑ አሸዋውን ወደዚያ ድንጋይና ጠጠር ሞልቶበት ወደነበረው ባሊ አፈሰሰው፡፡ አሸዋዎቹ ሹልክልክ እያሉ ባገኙት ቀዳዳ ሁሉ ገቡ፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ፣ “አሁንስ ባሊው ሙሉ ነው የምትሉ ስንት ናችሁ?” አሁን ተማሪዎቹ በሙሉ በአንድ ቃል፣ “ባሊው አሁንም አልሞላም” ብለው መለሱለት፣ አካሄዱ ገብቷቸው፡፡ አሰልጣኙ እንደገና ሌላ ውኃ የሞላበት ባሊ ከጠረጴዛው ስር በማንሳት ድንጋይ፣ ጠጠርና አሸዋ ሞልቶበት ወደነበረው ባሊ አፈሰሰውና በባሊው ውስጥ ሌላ ምንም ነገር መጨመር እስከማይቻል ድረስ ሞላው፡፡

የመጨረሻው ትምህርታዊ ጥያቄ እንዲህ የሚል ነበር፡፡ “ከዚህ ምሳሌ የምናገኘው ዋና ቁምነገር ምንድን ነው?” አላቸው፡፡ አንዱ ሰልጣኝ አጁን አውጥቶ፣ “ምንም እንኳ ጊዜህ በብዙ ነገር ቢጨናነቅ፣ አሁንም ሌላ ነገርን አጨናንቀህ ማድረግ እንደምትች ነው” አለው፡፡

አሰልጣኙም፣ “ተሳስተሃል! የዚህ ምሳሌ ዋነኛ ትምህርት በመጀመሪያ ትልልቆቹን ድንጋዮች ባሊው ውስጥ ባትጨምር ኖሮ ትንንሾቹን ጠጠሮች፣ አሸዋውንና ውሃውን መጨመር አትችልም ነበር፡፡ ትልልቆቹ ድንጋዮች የሚወክሉት በሕይወትህ ያሉትን ዋና ዋና የሕይወት አላማዎችና ግቦች ነው፡፡

ቤተሰብህ፣ ጤንነትህ፣ የትምህርትህ አቅጣጫ፣ ዋነኛ ሕልሞችህና የመሳሰሉት … ዋና ዋና ከሚባሉት “ድንጋዮች” መካከል ይገኛሉ፡፡ በመጀመሪያ በእነዚህ ነገር ካልተደላደልክና የሕይወትህን አቅጣጫ ካልሞላኸው፣ በጥቃቅን ነገሮች ተጨናንቀህ ሕይወትህን ታባክናለህ፡፡

አንዳንድ ሰዎች ጊዜን በአግባቡ የመጠቀምን ጥበብ ማዳበር በራሱ እጅግ አድካሚ ስራ ነው ብለው ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ሁኔታው የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ ዛሬ የሕይወቴን ዋና ዓላማ በመለየትና ቅድሚያን ለእርሱ በመስጠት መልክ የያዘ ሕይወት ለመኖር ማቀድ ካልቻልኩ ነገ በዚህና በዚያ የባከነውን ጊዜዬን መለስ ብዬ ከማየትና ከመቆጨት ውጪ ምንም ነገር ለማድረግ ያስቸግረኛል፡፡

ሠናይ ቀን!

@Ethiopiagna
2.0K views mïçkéŷ, 03:00
Open / Comment
2020-11-24 06:00:02 ስኬታማና ስኬት አልባ ሰዎች

>>ስኬት አልባ ሰዎች የችግሩ አካል ሲሆኑ ስኬታማዎቹ ደግሞ የመፍትሄው አካል ናቸው።

>>ስኬታማዎቹ እቅድ ሲኖራቸው ስኬት አልባዎቹ ደግሞ ምክንያት አላቸው፤

>>ስኬታማዎቹ ይህንን ላድርግ ሲሉ ስኬት አልባዎቹ ደግሞ ይህ የእኔ ስራ አይደለም ይላሉ፤

>>ስኬታማዎቹ ለእያንዳንዱ ችግር መፍትሄ ሲፈልጉ ተቃራኒዎቹ ደግሞ ለእያንድአንዱ መፍትሄ ችግሩን ይፈልጋሉ፤

>>ስኬታማዎቹ አስቸጋሪ ቢሆንም እንኳን ማድረግ እንደሚቻል ሲገልጹ ተቃራኒዎቹ ደግሞ ቢቻልም አስቸጋሪ መሆኑን ይገልጻሉ፤

>>ስኬታማዎቹ ስህተት ሰርተው ለስህተታቸው ሙሉ ሀላፊነት ሲወስዱ ሌሎቹ ደግሞ ጥፋቱ የእኔ አይደለም በማለት በህተታተቸው ላይ ሌላ ስህተት ይደርባሉ።

>>ስኬታማዎቹ መስዋእት ሲከፍሉ ተቃራኒዎቹ ደግሞ ቃል ብቻ ይገባሉ፤

>>ስኬታማዎቹ የሆነ ነገር ማድረግ ይገባኛል ሲሉ ተቃራኒዎቹ ደግሞ የሆነ ነገር ሊደረግ ይገባል ይላሉ፡፡

>>ስኬታማዎቹ የቅንጅቱ አካል ሲሆኑ ተቃራኒዎቹ ደግሞ ከቅንጅቱ ይርቃሉ
>>ስኬታማዎቹ አማራጮችን ሲፈልጉ ተቃራኒዎቹ ደግሞ ችግሮችን ይፈልጋሉ፤

>>ስኬታማዎቹ ስኬታማ መሆን የሚቻለው በጥረት መሆኑን ሲያምኑ ተቃራኒዎቹ ደግሞ ስኬታማ የሚሆነው በሌሎች ማጣት ላይ ተመስርቶ መሆኑን ያምናሉ፤

>>ስኬታማዎቹ መጻኢውን ሲመለከቱ እነዚያዎቹ ደግሞ ያለፈውን ይናፍቃሉ፤

>>ስኬታማዎቹ ሙቀት ፈጣሪዎች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ የሙቀቱ መለኪያዎቹ ይሆናሉ፤

>>ስኬታማዎቹ የሚሉትን በጥንቃቄ አስቀድመው ሲመርጡ ተቃራኒዎቹ ደግሞ የሚሉት የመጣላቸውን ነው፤

>>ስኬታማዎቹ ጠንካራ ክርክር ቀለል ባለ አገላለጽ ሲጠቀሙ ስኬት አልባዎቹ ደግሞ ቀላል ክርክር ነገር ግን በከባድ አገላለጽ ይጠቀማሉ፡

>>ስኬታማዎቹ በጥቅም ላይ ጠንካራ ሆነው ነገር ግን በሌሎች ቀላል ነገሮች ለመስማማት ዝግጁ ሲሆኑ እነዚያዎቹ ደግሞ በተራ ነገሮች ላይ ጠንካሮች ሆነው በጥቅም ላይ ግን ለመደራደር ዝግጅዎች ናቸው።

>>ስኬታማዎቹ ሌሎች በአንተ ላይ ሊያደርጉብህን የማትፈልገውን ነገር በሌሎች ላይ አታድርግ የሚለውን ፍልስፍና ሲከተሉ ደካማዎቹ ደግሞ የሚያምኑት ሌሎች በአንተ ላይ ከማድረጋቸው በፊት ቀድመህ አድርግባቸው የሚለውን ይከተላሉ።

>>ከየትኛው ወገን ናችሁ???

ሠናይ ቀን!

@Ethiopiagna
1.9K views mïçkéŷ, 03:00
Open / Comment
2020-09-29 05:07:58 ሀ ሁ ሂ ··· መርጌታ

ከፊደል ቤቱ ላይ አይኖቼን ተክዬ
የሀገሬን ባህል ታሪኳን ወክዬ

ከኣላዋቂዎች ፊት ማወቅን ከሚሹ ካሉበት ተስዬ
በቀጭኗ ዱላ ፊደል እየገረፍኩ ሀ ሲሉ ሀ ብዬ
ያልኩትን ሲደግሙ አሉ ከጉያዬ

ግና ይሄ አይምሮ ምንም የማያውቀው
ሀ'ን ሀ ስለው ብቻ ሀ ብሎ ላወቀው

ሀ ፐ ናት ብል ያኔ ፊደል ሳስቆጥረው
ፊደል ገበታውን በ ፐ እየጀመረ በ ሀ ነው የሚጥለው

በታዳጊ አይምሮ ሀ'ን ፐ የሚያደርገው
የሞተው እያለ ያልሞተው የሚያርገው

ድሮ ድሮ ያኔ በሀሰት መርጌታ ፊደል የቆጠረው
በ ሀ በ ፐ ፋንታ ጠጠር ያነጠረው
ዛሬ በቄስ ቤቱ
ከህፃናት ጋራ እውቀትን ሊለግስ
ሲሳሳት ይኖራል
በ ፐ' ታላቅ ክብር ሀ' ቤትን ሲያወድስ።

የዘመኑን አንዳንድ አስተማሪዎች ይመለከታል

የጊዜ ልጅ
@ethiopiagna
2.9K views...እናት ጊዜ..., edited  02:07
Open / Comment