🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

....አዲስ አበባ ላይ የሞተው የሕዝብ ቁጥር ዘጠኝ ሺህ ይኾናል ተብሎ ተገመተ። የኅዳር በሽታ (ግ | ኢትዮጵ

....አዲስ አበባ ላይ የሞተው የሕዝብ ቁጥር ዘጠኝ ሺህ ይኾናል ተብሎ ተገመተ።
የኅዳር በሽታ (ግሪፕ) በአዲስ አበባ ብቻ አልተወሰነም፤ ወደ ባላገርም ተላልፎ ብዙ ሰው ፈጅቷል። ኾኖም በባላገር የአዲስ አበባን ያኽል አልጠነከረም ይባላል። በዚህ በሽታ በመላ ኢትዮጵያ የሞተው ሕዝብ ቁጥር እስከ አርባ ሺህ ድረስ መገመቱን አስታዋለሁ።"
ምስሉ ፦አልጋ ወራሽ ተፈሪ ከበሽታው ካገገሙ በሁዋላ ከመኳንንቱ ጋር የተነሱት በ1911 ዓ/ም የአዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት በሽታውን በተመለከተ የሚከተለውን ማስታወቂያ አውጥቶ ነበር

የአዲስ ፡ አበባ ፡ ከተማ' ማዘጋጃ ቤት
=========================
ማስታወቂያ
1. ለዚህ ፡ ለዛሬ በሽታ ፡ ነጩን: የባሕር ፡ ዛፍ፡ ቅጠሉን: እየቀቀላችሁ ማታ ስትተኙ በላቦቱ ታጠኑ። ደግሞ ፡ የባሕሩን ዛፍና ቅጠል፡ እርጥቡን በብዙ ፡ አድርጋችሁ በቤታችሁም፡ ውስጥ ፡ በየደጃችሁም፡ እያነደዳችሁ አጭሱበት።
2. አይነ ምድራችሁን ሳትቆፍሩ አትቀመጡ ። እይነ ምድር፡ ተቀምጣችሁ ስትነሡ ፡ ባይነ ምድራችሁ ፡ ላይ ፡ የባሕር ፡ ዛፍ ፡ ቅጠል ጣሉበት። ያልጣላችሁበት እንደሆነ ከአይነ ምድራችሁ፡ ላይ ፡ እንደገና በሽታ ይነሣል።
3. ባትታመሙም፡ ብትታመሙም ፡ ውሀ ፡ እያፈላችሁ ፡ በውስጡ ጨው እየጨመራችሁ ፡ ጡዋትና፡ ማታ ፡ አፋችሁን ተጉመጥመጡ ።
4. ውሻ፣ ድመት፣ በቅሎና ፈረስ ሌላም ይህን የመሰለ፡ ሁሉ፡ በሞተባችሁ ጊዜ ሽታው በሽታ ያመጣል ና፡ ቅበሩት።
5. ሰው ፡ የሞተባችሁ፡ እንደህነ መቃብሩን ፡ በጣም ፡ አዝልቃችሁ ፡ ሳትቆፍሩ፡ አትቅበሩ ። በጣም ሳትቆፍሩ የቀበራችሁ ፡ እንደሆነ አውሬና ውሻ እያወጣ ይበላዋል። ሽታውም ከዛሪው የበለጠ በሽታ ያመጣብናልና።
6. በቤቱ፡ ሰው ፡ የታመመበት ሰው ፡ ወደ ፡ ማዘጋጃ ፡ ቤት፡ ድረስ፡ እየመጣ አለዋጋ መድኃኒቱን ይውሰድ። በማናቸውም ፡ ምክንያት፡ የሚያድን እግዚአብሔር፡ ነው ። ነገር፡ግን፡ የሚያድን ፡ እግዚአብሔር፡ ነው፡ ብሎ ፡ መድኃኒት አላደርግም ፡ ማለት እግዚአብሔርን መፈታተን ይሆናልና፡ መድኃኒት አናደርግም አትበሉ። መደኃኒትንም፡ የፈጠረልን፡ እግዚኣብሔር፡ ነው፡
7. ደግሞ ከመቃብር ላይ በሽታ እንዳይነሣ ብሎ መንግሥታችን በቸርነቱ፡ ብዙ፡ ኖራ በየቤተክርስቲያኑ አስቀምጥቶልናልና፥ በመቃብሩ ውስጥ ሬሳውን አግብታችሁ በላዩ ጥቂት አፈር ጨምራችሁ ባፈሩ፡ ላይ ኖራውን አልብሱና፡ከዚያ፡ በዋሁላ አፈር መልሱበት። ኖራው የሬሳውን ሽታ ያጠፋውና በሽታ፡ እንዳይነሣ ይሆናል።

ሕዳር፡፩፡፲፱፻፲፩ (1911 ዓ/ም)
አዲስ ኣበባ
የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዲረክተር፡ ኅሩይ፡ ወ : ሥ
(ተፈፀመ)


ጽንሰ ኢትዮጵያ ሐዳስ


#ለማንኛውም ሐሳብ እና አስተያየት
@Yottor_bot
ላይ ያድርሱን።