Get Mystery Box with random crypto!

#Update የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችው ፅጌሬዳ ግርማይን በመግደል የተከሰሰው ተማ | Freshman course

#Update

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችው ፅጌሬዳ ግርማይን በመግደል የተከሰሰው ተማሪ በ17 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ቤት ወሰነ።

ፍርድ ቤቱ ዛሬ ግንቦት 19/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን በወንጀል ህግ ቁጥር 5391-ሀ ጥፋተኛ አድርጎታል።

አቃቤ ህግ የቅጣት ማክበጃ የወንጀል ህግ ቁጥር 84 እና 86 መሠረት አድርጎ በደረጃ 38 ይወሰንልኝ ብሎ አቅርቧል።

የተከሳሽ ብሩክ በላይነህ ጠበቃ ተከሳሹ ይኖርበት በነበረው አካባቢ ጥሩ ፀባይ የነበረውና በበጎ አድራጎት ክበባት ተሳታፊ እንደነበር የፅሁፍ ማስረጃ በማቅረብ እንዲሁም ወንጀሉን የፈጸመው በወጣትነት ስሜት በመነሳሳት መሆኑን በመጥቀስ የቅጣት ማቅለያ አቅርበዋል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን የቅጣት ሃሳብ ካዳመጠ በኋላ ተከሳሹ ጥፋተኛ ከተባለበት እና ከሚያስቀጣው (18 ዓመት) አንድ ዓመት በመቀነስ በ17 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ጥር 23/2014 ዓ.ም የተገደለችው የ20 ዓመቷ ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት የ2ኛ ዓመት ተማሪ ነበረች፡፡

መረጃውን ያደረሱን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ መርኪያ መንገሻ ናቸው።

@tikvahuniversity