🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

#WoldiaUniversity በ2014 ዓ.ም በወልድያ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ የተመደ | Freshman course

#WoldiaUniversity

በ2014 ዓ.ም በወልድያ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ግንቦት 30 እና ሰኔ 01/2014 ዓ.ም
እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

• የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ካርድ ዋናውና ኮፒው
• ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና
ኮፒው
• የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት
ዋናውና ኮፒው
• 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ (4)
• ብርድልብስ፣ አንሶላና የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ የነበራችሁና በተለያየ ምክንያት ዳግም ቅበላ የሞላችሁ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ከአዲስ ገቢ ተማሪዎች ጋር ምዝገባ ማድረግ አለባችሁ ተብሏል።

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

@freshman_course
@freshman_course