Get Mystery Box with random crypto!

Doro wat ዶሮ ወጥ • አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች • 8 ስኒ የተከተፈ ሽንኩርት • 6 | ገበታ Recipes®

Doro wat
ዶሮ ወጥ

• አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
• 8 ስኒ የተከተፈ ሽንኩርት
• 6 (1/2) ውሃ
• 180 ሚሊ የቲማቲም ድልህ
• 2 ስኒ ንጥር ቅቤ
• 1 (1/2) ስኒ በርበሬ
• 1 የሻይ ማንኪያ የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት
• 1 የሻይ ማንኪያ የተፈቀፈቀ ዝንጅብል
• 6 አጥንቱ ያልወጣለት ቆዳው የተገፈፈ የዶሮ እግር
• 6 አጥንቱ ያልወጣለት ቆዳው የተገፈፈ የዶሮ ታፋ (አጭሬ አቋራጭ)
• 1 የሻይ ማንኪያ የተወቀጠ ኮረሪማ
• 1 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ቆንዶበርበሬ
• 1/2 ስኒ ጣፋጭ ነጭ ወይን
• 12 ተቀቅለው የተላጡ እንቁላሎች

• አሰራር
1. ሁሉንም ንጥረ ነገሮች መያዝ የሚችል ድስት ውስጥ ሽንኩርቱን መጨመርና ለብ ባለ እሳት ከ1 እስከ 1:30 ሰዓታት በግማሽ ስኒ ውሃ ማቁላላት (ሽንኩርቱ ወርቃማ እስኪሆን ድረስ ማቁላላት)።
2. የቲማቲም ድልሁን ጨምሮ ከ4-5 ደቂቃ በደንብ እስኪዋሃድ እያማሰሉ ማብሰል፤
3. ቅቤውን፣ በርበሬውን፣ ነጭ ሽንኩርቱንና ዝንጅብሉን መጨመር፤
4. ቅቤው ሲቀልጥ እሳቱን መቀነስና ለ1 ሰዓት ያክል አልፎ አልፎ እያማሰሉ ማብሰል፤
5. 30 ደቂቃ ሲሞላው ዶሮውን ማዘጋጀት መጀመር
6. መካከለኛ ድስት ውስጥ በሀይለኛ እሳት ለይ ዶሮውን ሊሸፍነው ከሚችል ውሃ ጋር መጣድ፤
7. ውሃው ሲፈላ እሳቱን ትንሽ ቀንሶ ለ15 ደቂቃ ማብሰል ከዛም አውጥቶ ማጥለሌ፤
8. የሽንኩርቱ ድብልቅ ሲበስል ዶሮውን ጨምሮ በአነስተኛ እሳት ለተጨማሪ 1 ሰዓት ማብሰል
9. የቀረውን 6 ስኒ ውሃ መጨመርና በጥንቃቄ ማማሰል
10. ወጡ ወፈር እስኪል ድረስ ለ15 ደቂቃ ማብሰል፤
11. ኮረሪማውን፣ ቁንዶ በርበሬውንና ወይኑን መጨመር፤
12. የተቀቀሉትን እንቁላሎች ጨምሮ ለ15 ደቂቃ አብስሎ ማውጣት።

@Gebeta_Recipes