Get Mystery Box with random crypto!

Banana cake ባናና ኬክ • ግብዓቶች • 5 እንቁላል • 3 የሾርባ ማንኪያ ቤ | ገበታ Recipes®

Banana cake
ባናና ኬክ

• ግብዓቶች

• 5 እንቁላል
• 3 የሾርባ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር
• 100 ሚሊ ሊትር ወተት
• 50 ሚሊ ሊትር ዘይት
• ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው
• 1 የሻይ ማንኪያ ቫኒላ
• ግማሽ ኪሎ ግራም የፉርኖ ዱቄት
• 3 የቡና ስኒ (300 ግራም) ስኳር
• ግማሽ ኪሎ ግራም ሙዝ

• አሰራር
1. ሙዙን ልጦና ከትፎ ከስኳሩ ጋር በዕንቁላል መምቻ እስኪወፍር ለረጅም ጊዜ መምታት፤
2. እንቁላሉን በዝግታ እየጨመሩ መምታት፤
3. ወተቱንና ዘይቱን ጨምሮ በደንብ ማዋሃድ፤
4. ጨዉን፣ ዱቄትና ቤኪንግ ፓውደር ጨምሮ ትንሽ ከመቱ በኳላ ቫኒላውን መጨመር፤
5. የኬክ መጋገሪያ ትሪ ላይ ቅቤ ቀብቶ ዱቄት በላዩ ከነሰነሱ በኋላ ዱቄቱን አራግፎ ውሁዱን መጨመር
6. የሞቀ የዳቦ መጋገሪያ ውስጥ በ220°c ለ45 ደቂቀ መጋገር ፤
7. ሲቀዘቅዝ እንደ አስፈላጊነቱ መጠቀም ።

@Gebeta_Recipes