Get Mystery Box with random crypto!

ሐምበርገር • ግብዓቶች • ግማሽ መካከለኛ ጭልፋ ደቆ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት •1 | ገበታ Recipes®

ሐምበርገር

• ግብዓቶች
• ግማሽ መካከለኛ ጭልፋ ደቆ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
•1 የሾርባ ማንኪያ ደቆ የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት
•ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው
•ግማሽ የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
•ግማሽ የቡና ሲኒ የፉርኖ ዱቄት
•ግማሽ የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ሮዝመሪኖ
• 300 ግራም የተፈጨ ቀይ ሥጋ
• 2 ዕንቁላል
• 4 የቡና ሲኒ (100 ግራም) የዳቦ ዱቄት
• ግማሽ የሻይ ማንኪያ የደቀቀ ፐርስሊ
•1 የሻይ ማንኪያ በርበሬ
•2 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
•2 ዝንጣፊ የሠላጣ ቅጠል
•3 ክብ የሐምበርገር ዳቦ ወይም 6 ተጠብሶ በቅቤ የወዛ ስስ ዳቦ
•3 በስሱ የተቆረጠ ክብ ቲማቲም

• አሰራር
1. ከዘይት፣ ከሠላጣ፣ ከዳቦውና ከቲማቲሙ በስተቀር ሌሎቹን ጥሬ ዕቃዎች በሙሉ ቀላቅሎ በደንብ በእጅ ማሸት፤
2. ሦስት ቦታ ከፍሎ በክብ ማድቦልቦልና መጠፍጠፍ ፤
3. በግሪል ወይም መጥበሻ ለይ በጋለ ዘይት መጥበስ፤
4. የተጠቀሙት ክቡን ዳቦ ከሆነ ከጎኑ በመቁረጥ ሁለት ቦታ ከፍሎ በቅቤ ማውዛት፤
5. አንዱ ቁራጭ ላይ የተጠቀሰውን ሥጋ ፣ ቀጥሎ የሠላጣ ዝንጣፊ ከዚያም አንድ ቲማቲም ካደረጉ በኃላ ሌላ ቁራጭ ዳቦ ከላይ መደረብ፤
6. በዚህ መልኩ ቀሪዎቹን አዘጋጅቶ መጨረስ፤
7.ከድንች ጥብስና ካሮት ጋር ሊቀርብ ይችላል።

@Gebeta_Recipes