Get Mystery Box with random crypto!

የካካዋ ብስኩት • ግብዓቶች • 200 ግራም የፍርኖ ዱቄት (4 የቡና ስኒ) | ገበታ Recipes®

የካካዋ ብስኩት

• ግብዓቶች
• 200 ግራም የፍርኖ ዱቄት (4 የቡና ስኒ)
• 200 ግራም ስኳር (4 የቡና ስኒ)
• 200 ግራም የገበታ ቅቤ ወይም ማርጋሪን
• 1 እንቁላል
• 2 የሾርባ ማንኪያ ካካዋ
• 2 የሻይ ማንኪያ ቫኒላ
• 2 የሻይ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር
• (1/2) ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው

• አሰራር
1. በቅድሚያ ኦቨኑን በ180° ሴንቲግሬድ ማሞቅ፤
2. በጎድጓዳ ሰሀን እንቁላል፣ ቫኒላ፣ የገበታ ቅቤ ወይም ማርጋሪን እና ስኳሩን ጨምሮ በደንብ መምታት፤
3. በሌላ ጎድጓዳ ሰሀን ዱቄቱን፣ ካካዋ፣ ቤኪንግ ፓውደሩንና ጨው ጨምሮ በደንብ ማዋሃድ፤
4. እንቁላሉን ወደ ዱቄቱ አደባልቆ በእጅ ማሸት፤
5. ሊጡ ከወፈረ በኋላ ንጹህ ጠረጴዛ ላይ አድርጎ በመዳመጫ ወይም በጠርሙስ መዳመጥ፤
6. የብስኩት ቅርጽ ማውጫ ወይም የቡና ስኒ በመጠቀም በክብ በክብ አድርጎ ማውጣት፤
7. ዘይት የተቀባ የብስኩት መጋገሪያ ትሪ ላይ አድርጎ ለ20 ደቂቃ መጋገር፤
8. ዙሪያው ቡናማ እስኪሆን ማብሰል፤ አውጥቶ ማቀዝቀዝ።

@Gebeta_Recipes