🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ቤት የሚሰራ የእንጆሪ አይስክሬም • ግብዓቶች • 1 የሻይ ማንኪያ ቫኒላ • 2 | ገበታ Recipes®

ቤት የሚሰራ የእንጆሪ አይስክሬም

• ግብዓቶች
• 1 የሻይ ማንኪያ ቫኒላ
• 200 ግራም እንጆሪ
• 3 እንቁላል
• 300 ሚሊ ሊትር ክሬም (6 የቡና ስኒ)
• 60 ግራም ስኳር (1 የቡና ስኒ እና 1 የሾርባ ማንኪያ)

• አሰራር
1. በትንንሽ ጎድጓዳ ሰሀን የእንቁላል አስኳል፣ ስካርና ቫኒላ ጨምሮ መምታት፤
2. በልላ ጎድጓዳ ሰሀን ክሬሙን ጨምሮ እስኪወፍር ድረስ መምታት፤
3. እንቁላሉን እና የተመታውን ክሬም በአንድ ላይ መቀላቀል እና ማዋሃድ፤
4. ሁለት ዕቃ አድርጎ ክሬሙን እኩል ለሁለት መክፈል፤
5. የሙዝ ኬክ መጋገሪያ ውስጥ የክሬሙን ግማሽ ጨምሮ ወደ ዲፕፍሪዝ ውስጥ አስገብቶ ለ1 ሰዓት ያህል ማቆየት፤
6. እንጆሪውን በጁስ መፍጫ ፈጭቶ የተፈጨውን እንጆሪ ወደ ክሬሙ ውስጥ መጨመር፤
7. በደንብ አደበላልቆ ከዲፐፍሪዘር አውጥቶ የእንጆሪ ክሬሙን መጨመር እና በደንብ አዳርሶ ለሌላ 2 ሰዓት ዲፕፍሪዝ ውስጥ ማድረግ፤
8. ማቅረብ ሲፈለግ ከዲፕፍሪዝ ውስጥ አውጥቶ በሰሀን ማቅረብ።

@Gebeta_Recipes