🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ቴላቴሊ • ግብዓቶች -ውሃ -ሩብ የሻይ ማንኪያ ጨው -400 ግራም ፉርኖዱቄት | ገበታ Recipes®

ቴላቴሊ

• ግብዓቶች
-ውሃ
-ሩብ የሻይ ማንኪያ ጨው
-400 ግራም ፉርኖዱቄት (8 የቡና ሲኒ)
-4 እንቁላል

• አሰራር
-ዱቄቱን እና ጨዉን ቀላቅሎ ጠረጴዛ ላይ ማስቀመጥ
-ዱቄቱን መሐሉን መክፈት,አንቁላል መጨመር እና በንጹህ እጅ ማሸት(ለአስር ደቂቃ መታሸት አለበት)
-እየታሸ እያለ ሊጡ የመድረቅና የመፈረካከስ ባህሪ ካመጣ ከ4 - 5 የሾርባ ማንኪያ ውሃ መጨመር
-ከታሸ በኋላ ለ15 ደቂቃ በፌስታል ተጠቅልሎ መቀመጥ አለበት
-ሊጡን በእንጨት ወይም በጠርሙስ ከሶስት ሴ.ሜ ውፍረት እና ከሀምሳ ሳንቲ ሜትር ቁመት እንዳይበልጥ አድርጎ መዳመጥ
-ተዳምጦ ካለቀለት በኋላ በግምት በአንድ ሳ.ሜ ርቀት በቢላዋ መቁረጥ
-ዱቄት የተነሰነሰበት ትሪ ወይም ጠረጴዛ ላይ በመዘርጋት ለአንድ ሰዐት ያህል መጠጥ እንዲል ማድረግ
-ሁለት ሊትር ውሃ አፍልቶ ጨው ጨምሮ ቴላቴሊውን ቀስ እያደረጉ ውሃ ውስጥ መጨመር
-ለሶስት ደቂቃ ያህል መቀቀል እና በፓስታ ማጥለያ አድርጎ ማጥለል
-ከተለያዩ አይነት ሶሶች ጋር ቀላቅሎ ማቅረብ

@Gebeta_Recipes