🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ክለብ ሣንድዊች • ግብዓቶች • 1 ኪሎ ግራም ዳቦ • 3 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቅቤ | ገበታ Recipes®

ክለብ ሣንድዊች

• ግብዓቶች
• 1 ኪሎ ግራም ዳቦ
• 3 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቅቤ
• 4 የሾርባ ማንኪያ (100 ግራም) ማዮኔዝ ሶስ
• 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) ተቀ ቅሎ የተከተፈ የዶሮ ሥጋ
• 1 መካከለኛ ጭልፋ (100 ግራም) የተከተፈ ቲማቲም
• 2 መካከለኛ ጭልፋ (100 ግራም) የተከተፈ የሠላጣ ቅጠል
• 1 መካከለኛ ጭልፋ (100 ግራም) የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
• 3 በቁመቱ የተከተፈ ቃርያ
• 4 ተቀቅሎ በቁመቱ የተከተፈ ዕንቁላል
• 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) በቁመቱ የተከተፈ ለስላሣ የበሬ ስጋ
• 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
• 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
• 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) በቁመቱ የተከተፈ ሞርቶዴላ

• አሰራር
1. ጥሬ እቃዋቹን በሙሉ ከዳቦ በስተቀር ጋር ቀላቅሎ መለወስ፤
2. ካሬ ዳቦውን በጎኑ በስሱ መቁረጥ፤
3. የያንዳንዱን ቁራጭ ጠብሶ አንዱን ገፅታ በቅቤ ማውዛት፤
4. ሦስት የሾርባ ማንኪያ ዉሁድ ባንድ ቁራጭ የወጣ ገፅታ ላይ አድርጎ በቢለዋ እየተጫኑ ማስተካከል ፤
5. በላዮ አንድ ቁራጭ ዳቦ መደረብና ከውሁዱ ሦስት የሾርባ ማንኪያ ጨምሮ ማስተካከል ፤
6.ተጨማሪ አንድ ቁራጭ መደረብና ጫን ፡ጫን አድርጐ ማስተካከል ፤
7.ዙሪያውን በቀጭኑ በቢለዋ እየከረከሙ ማስተካከል፤
8.የተደራረበውን ዳቦ ከላይኛው ግራ ማእዘን ጫፍ በመጀመር ቀኝ ማዕዘኑ ድረስ በቢለዋ መቁረጥ፤
9.ቀጥሎ ከላይኛው ቀኝ ማዕዘን ጫፍ በመጀመር ግራ ማዕዘኑ ድረስ በቢለዋ መቁረጥ፤
10.በዚሕን ጊዜ አራት ባለ ሦስት ማዕዘን ሳንድዊች ስለሚኖሩን እያንዳዳቸዉን በስቴኬኒ ወግቶ ማያያዝ፤
11.በለሣሕን ለይ አራቱንም ሳንዲዊቾች ካንድ ዝንጣፌ ሰላጣና ከድንች ጥብስ ጋር አድርጎ ማቅረብ፤
12.በዚሕ መልኩ የቀረበዉን ወሁድና ዳቦ እያዘጋጁ መቀጠል ይቻላል።
( ለክለብ ሳንዲዊች ማዘጋጃነት የሚውሉ ጥሬ ዕቃዋች ከተለወሱ በኋላ መቀመጥ አይችሉም ። ሳይለወሱ ለየብቻ ማቀዝቀዣ ዉስጥ አስቀምጦ ሲፈልጉ ለውሶ መጠቀም ይገባል።)

@Gebeta_Recipes