🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

Ricotta cheese cake የሪኮታ ቺዝ ኬክ • ግብዓቶች • 600 ግራ | ገበታ Recipes®

Ricotta cheese cake
የሪኮታ ቺዝ ኬክ

• ግብዓቶች
• 600 ግራም ሪኮታ(ቺዝ)
• (1/2) ሩብ የሾርባ ማንኪያ ጨው
• 80 ግራም የተፈጨ ስኳር (1 የቡና ስኒ እና 3 የሾርባ ማንኪያ)
• 5 የሾርባ ማንኪያ ፍርኖ ዱቄት
• 20 ግራም ዘቢብ (2 የሾርባ ማንኪያ)
• 3 እንቁላል

• አሰራር
1. በቅድሚያ ኦቨኑን በ180° ሴንቲግሬድ ማሞቅ፤
2. ሪኮታውን በደንብ ውሃውን እስከሚጨርስ ድረስ ማጥለል፤
3. በጎድጓዳ ሰሀን የእንቁላል አስኳሉንና ነጩን መለየት፤
4. ነጩን እንቁላል ጨው ጨምሮ ነጭ እስከሚሆን ድረስ በደንብ መምታት፤
5. አስኳሉን፣ ስኳርና ቫኒላ ጨምሮ በደንብ መምታት፤
6. በትልቅ ጎድጓዳ ሰሀን ሪኮታውን፣ ዱቄቱንና ዘቢቡን ጨምሮ በደንብ ማደበላለቅ፤
7. የተመታውን የእንቁላል አስኳል እና ነጩን ቀላቅሎ በደንብ ማዋሃድ፤
8. የተዋሃደውን እንቁላል፣ ሪኮታና ዱቄት ውስጥ በደንብ እያዋሃዱ መቀላቀል፤
9. ክቡን የኬክ መጋገሪያ ፓትራ ዘይትና ዱቄት መቀባት፤
10. የተደበላለቀውን (የተዋሃደውን/ ሊጥ መጋገሪያ ውስጥ በመጨመር ለ35 ደቂቃ መጋገር፤
11. አውጥቶ ማቀዝቀዝ።

@Gebeta_Recipes