🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ስፓጌቲ ዊዝ ቺዝ • ግብዓቶች • 4 የሾርባ ማንኪያ (100 ግራም) የገበታ ቅቤ | ገበታ Recipes®

ስፓጌቲ ዊዝ ቺዝ

• ግብዓቶች
• 4 የሾርባ ማንኪያ (100 ግራም) የገበታ ቅቤ
• ግማሽ ኪሎ ግራም ፓስታ
• 2 መካከለኛ ጭልፋ የተፈጨ (200 ግራም) ቺዝ
• ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው
• 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
• 2 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
• አሰራር
1. ጎድጎድ ያለ ብረት ድስት ውስጥ በርከት ያለ ውሃ፣ ጨውና ዘይት መጣድ፤
2. ሲፈላ ፓስታውን እየበታተኑ መጨመር፤
3. ለሩብ ሰዓት ያህል እያማሰሉ ማብሰል፤
4. ሰፋ ባለ የፓስታ ማጥለያ አንጠፍጥፎ ማጥለል፤
5. ብረት ድስት ውስጥ ጨምሮ ወይም መጥበሻ ላይ አድርጎ ለሰስ ያለ እሳት ላይ መጣድ፤
6. ቺዝ፣ ቅቤና ቁንዶ በርበሬውን ጨምሮ ካስተካከሉ በኋላ ለውሶ ለገበታ ማቅረብ።

@Gebeta_Recipes