🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ቸኮሌት ጄነዋስ ኬክ • ግብዓቶች • 1 የቡና ስኒ (50 ግራም) የካካዎ ዱቄት | ገበታ Recipes®

ቸኮሌት ጄነዋስ ኬክ

• ግብዓቶች
• 1 የቡና ስኒ (50 ግራም) የካካዎ ዱቄት
• 4 የሾርባ ማንኪያ (100 ግራም) የገበታ ቅቤ
• 2 የሾርባ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር
• 8 እንቁላል
• 2 የቡና ስኒ (200 ግራም) ስኳር
• 3 የቡና ስኒ (150 ግራም) የፉርኖ ዱቄት
• አሰራር
1. እንቁላሉንና ስኳሩን ጎድጎድ ያለ እቃ ውሰጥ አድርጎ የሞቀ ውሃ የተጣደበት ብረት ድስት ውስጥ በማድረግ በእንቁላል መምቻ እጥፍ ያክል እስኪነሣ መምታት፤
2. ጎድጎድ ያለውን ዕቃ ከብረት ድስት ውስጥ ማውጣት፤
3. ዱቄቱን፣ ቤኪንግ ፓውደሩንና የካካዎ ዱቄቱን ለብቻ መቀላቀል ፤
4. በተጓዳኝ የኬክ መጋገሪያ ትሪ ላይ ትንሽ ቅቤ ቀብቶ ትንሽ የፉርኖ ዱቄት ላዩ ላይ ከነሰነሱ በኋላ ትሪውን በማንቀሳቀስ በእጅ ሳይነኩ አዳርሶ ዱቄቱን ማራገፍ፤
5. የቤኪንግ ፓውደሩንና ዱቄቱን ድብልቅ ቀስ በቀስ ላዩ ላያ በተን እያደረጉ በዝርግ ጭልፋ ወይም በእጅ ማዋሃድ ፤
6. ቅቤውን አቅልጦ በመጨመር ማዋሃድ፤
7. የተዘጋጀው የኬክ መጋገሪያ ላይ ውሁዱን ገልብጦ የሞቀ ዳቦ መጋገሪያ ውስጥ ማብሰል ወይም ከ200°c እስከ 220°c ለ30 ደቂቃ ማቆየት።
[በዚህ መልክ የተዘጋጀውን ብቻውን መብላት የሚቻል ሲሆን፣ ለተለያዩ የኬክ ዓይነቶች ማዘጋጃነትም ይውላል።]

@Gebeta_Recipes