Get Mystery Box with random crypto!

የቱና ትራሜዚኒ Tuna Tramezzini • ግብዓቶች • 2 የሻይ ማንኪያ | ገበታ Recipes®

የቱና ትራሜዚኒ
Tuna Tramezzini

• ግብዓቶች
• 2 የሻይ ማንኪያ ፐርስሊ
• 4 የሾርባ ማንኪያ ማዮኔዝ
• ሰላጣ
• 8 ስላይስ የተደረገ ዳቦ
• ጨውና ቁንዶበርበሬ
• 150 ግራም ቱና (2 ትንንሽ ቆርቆሮ የታሸገ ቱና)
• 2 ፍሬ ቲማቲም
• 1 ሎሚ ጭማቂውን
• አሰራር
1. ቱናውን ቆርቆሮውን ከፍቶ ዘይቱን ማጥለል፤
2. ቲማቲሙን አጥቦ በደቃቁ መክተፍ፤
3. ቱናውን ጎድጓዳ ሰሀን ውስጥ አድርጎ ቲማቲሙን መጨመር፤
4. ፐርስሊውን በደቃቁ ከትፎ መጨመር፤
5. ሎሚ፣ ማዮኔዝ፣ ጨውና ቁንዶበርበሬ አድርጎ ሁሉንም በደንብ ማደባለቅ፤
6. ሁለት ስላይስ ዳቦ አዘጋጅቶ በሁለቱም በኩል ማዮኔዝ መቀባት፤
7. የተቀላቀለውን ቱና በዳቦው በአንድ በኩል ላይ አስቀምጦ ቱናውን ማዳረስ፤
8. ሁለተኛውን የዳቦ ስላይስ ቱና የያዘው ስላይስ ላይ መደረብ፤
9. ሁሉም ሳንድዊች ተሰርቶ ካለቀ በኋላ እስከሚበላ ድረስ ዳቦው እንዳይደርቅ በጥቂቱ ረጠብ ያለ የኪችን ፎጣ ሸፍኖ ማስቀመጡ ይመረጣል።

@Gebeta_Recipes