Get Mystery Box with random crypto!

ክሬፕ ሱዜት Crepe suzette • ግብዓቶች • 2 ፍሬ ብርቱካን • 2 መለ | ገበታ Recipes®

ክሬፕ ሱዜት
Crepe suzette

• ግብዓቶች
• 2 ፍሬ ብርቱካን
• 2 መለኪያ የአናናስ አረቄ
• 4 ክሬፕ ቂጣ
• 4 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቅቤ
• 4 የሻይ ማንኪያ ስኳር
• 2 ብርቱካን ጁስ
• አሰራር
1. የክሬፕ ቂጣውን በቅድሚያ ማዘጋጀት፤
2. ብርቱካኑን መጭመቅ፤
3. ሁለቱን ብርቱካን ልጦ እያንዳንዱን መፈልቀቅ፤
4. በፍልቃቂው ላይ ያሉትን ቆዳዎች መላጥ፤
5. በመጥበሻ ላይ ቅቤውን ማቅለጥ፤
6. የተፈለቀቀውን ብርቱካን መጨመርና ስኳር ከላዩ ላይ መነስነስ፤
7. የብርቱካን ጁሱን እና የአናናስ አረቄውን ጨምሮ አልኮሉ በደንብ እስኪቃጠል ድረስ ማብሰል፤
8. የተሰራውን ክሬፕ ከተሰራው የብርቱካን ሶስ ላይ ማድረግ፤
9. ትንሽ ከሞቀ በኋላ ክሬፑን አንሰቶ ሶሱን ከላይ መጨመር፤
10. ለሁለት ቆርጦ ማቅረብ።

@Gebeta_Recipes