Get Mystery Box with random crypto!

ፍራይድ ቺክን • ግብዓቶች • 1 የሻይ ማንኪያ ጨው • 2 የቡና ስኒ (100 ግ | ገበታ Recipes®

ፍራይድ ቺክን

• ግብዓቶች
• 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
• 2 የቡና ስኒ (100 ግራም) የፉርኖ ዱቄት
• 5 የተመታ ዕንቁላል
• 1 ዶሮ (ከ800 ግራም እስከ 1 ኪሎ ግራም የሚመዝን)
• 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
• 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ዘይት
• 4 የሾርባ ማንኪያ (100 ግራም) የገባበት ቅቤ

• አሰራር
1. ዶሮውን መበለትና ማፅዳት፤
2. እያንዳንዱን ክፍል በሥጋ መቀጥቀጫ ጠፍጠፍ አድርጎ ማዘጋጀት፤
3. የፉርኖ ዱቄት፣ ጨውና ቁንዶበርበሬውን መቀላቀል፤
4. የዶሮውን ስጋ በተዘጋጀው ዱቄት መለወስ፤
5. እያንዳንዱን የተመታው እንቁላል ውስጥ እየነከሩ ወዲያውኑ በጋለ ዘይት መጥበስ ፤
6. ሥጋውን ትሪ ላይ መደርደር፤
7. ቅቤውን ቡናማ መልክ እስኪያወጣ አቅልጦ ላዩ ላይ ማፍሰስ።

@Gebeta_Recipes