Get Mystery Box with random crypto!

ማረፊያ፣ ጥንካሬ ወይስ ድክመት? አንዳንዴ ደካማ ጎናችን ጥንካሬያችን ይሆናል። ለምሳሌ ያህል የ | ስለ መፅሀፍት በጥቂቱ

ማረፊያ፣
ጥንካሬ ወይስ ድክመት?
አንዳንዴ ደካማ ጎናችን ጥንካሬያችን ይሆናል። ለምሳሌ ያህል የአንድ ህጻንን ታሪክ እንመልከት። ህጻኑ
የአስር አመት ልጅ ሲሆን በደረሰበት የመኪና አደጋ ግራ እጁን አጥቷል። እናም የአካል ጉዳት ቢኖርበትም
ጁዶ (የትግል ስፖርት አይነት) መሰልጠን ፈለገ።
ልጁም ወደ አንድ ጃፓናዊ የጁዶ አሰልጣኝ ሽማግሌ ዘንድ ሄደ። ስልጠናውንም ጀመረ። ልጁ ስልጠናውን
በሚገባ ቢያካሂድም፣ ለሶስት ወራት በተከታታይ መምህሩ የሚያስተምረው የጁዶ እንቅስቃሴ አንድ
አይነት ብቻ ነበር። ተማሪውም ይሄ ለምን እንደሆነ አልገባውም።
“ሰንሴ” አለ፣ ተማሪው በመጨረሻ “ሌላ እንቅስቃሴ መማር የለብኝም?”
“የምታውቀው ይህንን እንቅስቃሴ ነው፤ የሚያስፈልግህም ይሄ ብቻ ነው።” መምህሩ መለሰ፡፡
አልገባውም ሆኖም መምህሩን በማመን ስልጠናውን ቀጠለ።
ከጥቂት ወራት ስልጠናም በኋላ መምህሩ ተማሪውን ወደ መጀመሪያ ፍልሚያው ይዞት ሄደ።
የመጀመሪያዎቹን ሁለት ፍልሚያዎች ለእሱም እስኪገርመው ድረስ በቀላሉ አሸነፈ። ሶስተኛው
ፍልሚያው ፈታኝ እና አዳጋች ነበር፤ ሆኖም ተፋላሚው ትግስት በማጣቱ እና በመዳከሙ በሚያውቃት
አንድ እንቅስቃሴ ፍልሚያውን አሸነፈ። ስኬቱ ለእርሱም ደንቆታል፤ ወደ ፍጻሜም አለፈ።
አሁን ተፋላሚው እንደቀድሞዎቹ ተፋላሚዎች አልነበረም፤ ግዙፍ፣ ጠንካራ እና ልምድ ያለው ነው።
ለጥቂት ጊዜም ፍልሚያው ከልጁ ቁጥጥሩ ውጪ ሆነበት። ዳኛውም እረፍት እንዲወስዱ ጠየቃቸው።
“አይ” አለ መምህሩ፣ “ይቀጥል”
ፍልምያውም ቀጠለ፤ ተፋላሚው ድንገት ስህተት ሰራ፤ ልጁም የሚያውቃትን እንቅስቃሴ ተጠቅሞ
ተጋጣሚውን ዘረረው። ልጁም ፍልሚያውን እና ውድድሩን አሸነፈ። ዋንጫውንም አነሳ።
መምህሩ እና ልጁም ከውድድር ስፍራው ወደ ቤታቸው እየተመለሱ ሳለ፣ ሰለ እያንዳንዱ የፍልሚያ
ቅጽበቶች መወያየት ጀመሩ። በመሃልም ተማሪውም ድፍረቱን አሰባሰበና አንድ ጥያቄ ጠየቀ
“ሰንሴ፣ እንዴት በአንድ እንቅስቃሴ ብቻ ውድድሩን አሸነፍኩ?”
“ያሸነፍከው በሁለት ምክንያቶች ነው” መምህሩ መለሰ፣ “የመጀመሪያው፣ እጅግ ከባድ የሆነውን የጁዶ
እንቅስቃሴ በደንብ ለምደኸዋል። ሁለተኛው ምክንያት፣ ተፋላሚህም ይህንን እንቅስቃሴ መመከት
የሚችለው ግራ እጅህን በመያዝ ብቻ ነው።”
የልጁ ትልቁ ድክመቱ ጥንካሬው ሆነ።
በጸጋ መቀበልን ልመድ፣ ድክመትህንም ጥንካሬህ አድርገው።
ከጭንቅላትህን አፅዳ መጽሐፍ የተወሰደ
t.me/guramaylebooks