🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ትንሿን ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ማንበብ ያለባችሁ ለምንድን ነው? ፩. ስለ ጋብቻ በአበው ትምህርት | ስለ መፅሀፍት በጥቂቱ

ትንሿን ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ማንበብ ያለባችሁ ለምንድን ነው?

፩. ስለ ጋብቻ በአበው ትምህርት የዳበረ ነገረ መለኮታዊ ትምህርት ታገኙበታላችሁ፡፡

፪. በየዘመናቱ በጋብቻ ዙሪያ የነበሩት የምንፍቅና ትምህርቶች ከእነ መልሶቻቸው ታውቁበታላችሁ፡፡

፫. ከልማዳዊ ጋብቻ (ትዳር) በተለየ ብልጫ ያለው ኦርቶዶክሳዊ ትዳር እንድትኖሩ ይመራችኋል፡፡

፬. አንድ ወጣት ለማግባት እስከሚያስብ ድረስ ድንግልናውን ለምን መጠበቅ እንዳለበትና እንዴት መጠበቅ እንዳለበት ትምህርት ይሰጣል፡፡

፭. የማግባት አሳቡ ሲመጣ ወጣቱ መጀመሪያ ምን ማድረግና ማወቅ እንዳለበት፣ የትዳር አጋሩን ለመፈለግ የትና ምን ምን ነገሮችን ማድረግ እንዳለበት፣ ከምን መጠንቀቅም እንደሚያስፈልገው ያሳያል፡፡

፮. የትዳር አጋር ያላገኙ ወጣቶች እግዚአብሔር ለእነርሱ ያለው አሳብ ምን እንደ ኾነ አዲስ ምልከታና ምሪት ይሰጣል፡፡

፯. አጣማሪያቸውን ያገኙ ወጣቶች የዕጮኝነታቸውን ሕይወት እንዴት ማሳለፍ እንዳለባቸው ይመራል፡፡

፰. ሰርጋቸውን የትና እንዴት ማከናወን እንዳለባቸውና ከምን ዓይነት ቫይረስ ሊጠብቁት እንደሚኖርባቸው ያመለክታቸዋል፡፡

፱. ከሰርግ ማግስት ያለው ሕይወታቸው እንዴት ትንሿን ቤተ ክርስቲያን ማነፅ እንዳለባቸውና በዚያ ውስጥ ምንና እንዴት መጸለይ፣ መማር፣ መመጽወት፣ መፆም እንዳለባቸው፥ በአጠቃላይ እንዴት በቤታቸው ድኅነታቸውን መፈፀም እንዳለባቸው አርአያነት ባላቸው ቤተ ሰቦች ልምድ የዳበረ ትምህርትና ምሪት ያገኙበታል፡፡

፲. ባለ ትዳሮች በትዳር ሕይወታቸው ውስጥ የሚያጋጥሟቸው ፈተናዎች ምን ምን እንደ ኾኑና በምን ዓይነት አተያይ ሊፈቷቸው እንደሚችሉና እንደሚገባቸውም በዝርዝር መፍትሔ አሳቦች ይቀስሙበታል፡፡

፲፩. ወላጆች ልጆቻቸውን እንዴት ማሳደግ እንደሚኖርባቸው፥ እስከ አሁን ከሰማናቸውና ካነበብናቸው በተለየ አቀራረብ ጥልቅና ዝርዝር የኾኑ ትምህርቶችንና ልምዶችን ያውቁበታል፡፡

፲፪. ይህ መጽሐፍ፥ አይኾንም እንጂ 10 ሚልዮን ቅጂ እንኳን ቢሸጥ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ. ምእመናን 10 ሚልዮን ስላልኾኑ፥ ወደ ሌሎቹ መድረስ የምንችለው በአሠራር ነው፡፡ ስለዚህ ወደ ቀሪዎቹ እንዴት መድረስ እንደምንችልና ይህን ብናደርግ ምን ምን ጠቀሜታዎችን እንደምናገኝ ውጥን ምክረ አሳብን ይጠቁማል፡፡ በመጽሐፉ በጥቆማ መልኩ የቀረበ ቢኾንም፥ ዝርዝር አተገባበሩ በጸሐፊው እጅ ይገኛል፡፡

፲፫. በአጠቃላይ መጽሐፉን ማንበብ ያለብዎት እንዲሁ ከመቆጨት ባሻገር ለራስዎ፣ ለቤተ ክርስቲያንዎና ለሃገርዎ መሬት የረገጠ ሥራ ተቀናጅቶ ለመሥራት ነው፡፡