🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ገርጂ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን

Logo of telegram channel gerjimuluwongelchurch — ገርጂ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
Logo of telegram channel gerjimuluwongelchurch — ገርጂ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
Channel address: @gerjimuluwongelchurch
Categories: Uncategorized
Language: English
Subscribers: 190

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


The latest Messages

2023-04-16 11:08:04 የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!

“አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።”( 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥20)
ውድ የገርጂ ሙሉ ወንጌል አባላትና አገልጋዮች በሙሉ እንኳን ጌታ በሰላም ጠብቆ ለ2015 ዓመተ ምሕረት የትንሳኤው በአል መታሰቢያ አደረሳችሁ !!
ትንሳዔውን ስናከብር የጌታ ኢየሱስ ሞትና ትንሳዔ ምን እንዳስገኘልን በማሰብ ለጌታችን ክብርን እየሰጠን ሊሆን ይገባል። መጽሐፍ ቅዱሳችንን እንደሚነግረን በጌታ ኢየሱስ ሞትና ትንሳዔ ያገኘናቸው ብዙ ትሩፋቶች ስላሉ እነዚህን የሞቱና የትንሳኤውን ትሩፋቶች ከቅዱስ ቃሉ በመረዳትና በመኖር ሊሆን ይገባል።የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ካስገኘልን ቁልፍ ትሩፋቶች መካከል ጥቂቶቹ :-
1ኛ) ኃጢአት:  ሞትና ሲኦል በትንሳኤው ጌታ ተሸንፎአል።
ሞት ሆይ መውጊያህ የታል ሲኦል ሆይ ድል መንሳትህ የታል ተብሏል ።(1ቆሮ 15:55)
ሀጢአትና ሞት የሸነፉት በትንሳኤው ጌታ ብቻ ስለሆነ በጌታ ስም ያመኑ ብቻ ናቸው አሸናፊ ሆነው የሚመላለሱት ።ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶ ከመነሳቱ በፊት ሀጢያትና ሞት ብዙዎችን የሰው ልጆች ሲያሸንፉና ሲውጡ ኖረዋል።በጌታ በኢየሱስ ብቻ ተሸንፈዋል።እኛም በወደደን በእሱ አሸናፊዎች ሆነናል።
2ኛ) ትንሳኤ አስገኘልን :- ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን አሸንፎ የተነሳ ጌታ በመሆኑ ለእኛም ትንሣኤና ህይወት ሆኖልናል ። ኢየሱስ ክርስቶስ በኀጢአት ለሞትነው ሕይወት በእሱ ለሚያምን ሕያውነት ሰጥቷል። (ዮሐንስ 11:25)
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሳቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠቅም ለማያልፍም ርስት እንደ ምህረቱ ብዛት ዳግም ልደት ሰጠን።(1ጴጥ1:3-11)
ኢየሱስ ክርስቶስን ከሙታን ያስነሳው መንፈስ ከአማኞች ጋር ሕያው ሆኖ ይኖራል በአማኞችም ውስጥ ይሰራል ።(ኤፌ1:19-20)
3ኛ) በሞቱ የኃጢአት መስዋዕትና ማስተሰረያ
ለሰው ዘር በሙሉ ሆኗል ።ኢሳ53:1
ለአንዴና እና ለዘላለም ብቸኛው የኀጢአት መሰዋዕትና ማስተስረያ ሆኗል።ሮሜ 3:25
4ኛ) ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀን።ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን ጥል አስወግዶታል።እርቅንም አምጥቷል።(2ቆሮ 5:19)
ከእግዚአብሔር ጋር ለመታረቅ ከኃጢአተኛው የሰው ልጅ የሚጠበቀው በኢየሱስ ቤዛነት አምኖ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ብቻ ነው ።
5ኛ) መዋጀት :- የሰው ልጅ በኀጢአት ውድቀት ምክንያት ከእግዚአብሔር ተለይቶ ሳለ እግዚአብሔር በክርስቶስ ቤዛነት ትልቅ ዋጋ ከፍሎ እንደገና ሰውን ወደራሱ መለሰው።ይህም የእግዘብሔርን የሰውን ልጅ በኃጢአት ከጠፋበት መልሶ የራሱ ያደረገበት የመዋጀት ሥራ በክርስቶስ ሞት የተገኘ ድል ነው ።(ገላትያ 3:13)
በመጨረሻም ኑሮአችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ተመልሶ ይመጣል የሚለውን የተስፋ ቃል ሁል ጊዜ በማሰብና በመዘጋጀት ሊሆን ይገባል። ጌታ ዳግመኛ ሲመጣ በስሙ ያመኑትን አምነው የፀኑትን ይወስዳቸዋል። (ዮሐ 14:1-2)አማኞች የእርሱን ዳግም ምጽአት በቅድስናና በፍቅር ሆነን እየጠበቅን ከተሰጠን የወንጌል ተልዕኮ አንጻር የምስራቹን በጨለማ ላሉት እያበሰርን ለዓለም ጨውና ብርሃን ሆነን ልንመላለስ ይገባናል።(1ጴጥ 2:9-10)
እንደተናገረው ጌታ በቶሎ ይመጣል !!
አሜን ማራናታ !!!
መልካም የትንሳኤ በአል መታሰቢያ ለእናንተና ለቤተሰቦቻችሁ እንዲሆን ከልብ እንመኛለን ::

ከገርጂ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ የመሪዎች ጉባዔ
107 viewsedited  08:08
Open / Comment
2023-04-16 01:51:48 1ኛ ጴጥሮስ 1 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ፤ እርሱ ከታላቅ ምሕረቱ የተነሣ በኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሣት ምክንያት ለሕያው ተስፋ በሚሆን አዲስ ልደት፣
⁴ እንዲሁም በሰማይ ለማይጠፋ፣ ለማይበላሽና ለማይለወጥ ርስት እንደ ገና ወለደን።
⁵ እናንተም በመጨረሻው ዘመን ሊገለጥ የተዘጋጀው ድነት እስኪመጣ ድረስ በእምነት አማካይነት በእግዚአብሔር ኀይል ተጠብቃችኋል።
53 views22:51
Open / Comment
2023-04-13 21:18:21
ተፈፀመ
አርብ 11:00 ሰዓት

@GerjiYouth
53 views18:18
Open / Comment
2023-04-02 15:10:22
58 views12:10
Open / Comment
2023-04-01 13:30:05
95 views10:30
Open / Comment
2023-03-31 18:43:42
57 views15:43
Open / Comment
2023-03-30 16:47:10
158 views13:47
Open / Comment
2023-02-27 17:21:55 ለአገልግሎት ዘርፍ አስተባባሪዎች በሙሉ :-
የጌታ ሰላምና ፀጋ ለእናንተ ይሁን እያልን የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 25/2015 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሰአት የ6 ወራት የአገልግሎት አፈፃፀም ሪፖርታችሁን የምታቀርቡ ስለሆነ ሰአት አክብራችሁ እንድትገኙ በአክብሮት ትጠይቃላችሁ ።ተባረኩ
51 views14:21
Open / Comment
2023-01-20 22:49:37 ጥር 11/2015 የገርጂ ሙሉ አጥቢያ ጠቅላላ አገልጋዮች ስልጠና በዶ/ር አስቻለው አበበ
ክፍል 1
100 views19:49
Open / Comment
2023-01-20 22:46:31
104 views19:46
Open / Comment