🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የአዲስ አበባ ከተማ እና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ነዋሪዎች በነገው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አሸባ | Find Job In Ethiopia

የአዲስ አበባ ከተማ እና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ነዋሪዎች በነገው ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀውን ህወሀትን የሚያወግዝ እና መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ የድጋፍ ሰልፍ በመስቀል አደባባይ ያካሂዳሉ፡፡

በመሆኑም ነገ ከለሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ በዚህም መሰረት፦
ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎፒያ አደባባይ፣
ከመገናኛ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኔዓለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ፣
ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት፣
ከቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ እና አገር አስተዳደር መብራት ወይም ኢሚግሬሽን፣
ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ፣
ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ የኋላ በር፣
ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ
ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አጎና ሲኒማ እና አራተኛ ክፍለ ጦር
ከጦር ኃይሎች፣ ልደታ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ
ከጦር ኃይሎች ወደ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ፣ ሜክሲኮ፣ ለገሀር የሚወስደው መንገድ ለገሃር መብራት አካባቢ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

በተጨማሪም ከዋዜማው ምሽት ጀምሮ ሥነ- ስርዓቱ በሚከናወንበት እና ዝግ በሚሆኑ መንገዶች አካባቢ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው ተብሏል።