🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

እወዳታለው ፣ የምር......... የጠወለገች አበባ የውሃ ጠብታ እንደምትናፍቅ ፣ በጨለማ የ | ቅኔ ያለው ትውልድ

እወዳታለው ፣ የምር.........

የጠወለገች አበባ የውሃ ጠብታ እንደምትናፍቅ ፣ በጨለማ የከረመ ሰው የብርሃን ቅንጣትን እንደሚናፍቅ ፣ የራበው ህፃን የእናቱን ጡት እንደሚናፍቅ ሁሉ የእኔም ልብ የሷን ፍቅር ይናፍቃል ......

እሷ ግን ይህንን እውነት አትውቅም ። ማነው ስሙ ? አላውቀውም ። እና የማታውቂውን ሰው ነው ወደሽ ነው የምትሰቃይው ?........ እኔን የያዘኝ እኮ የአይን ፍቅር ነው ፤ ከእሱ ምን አለኝ ። የት ነው የምታውቂው ? ........ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ነበር የምንማረው ።......ለምን ወደድሽው ? ................. እኔንጃ ፤ ዝምታው ፣ ምናልባትም ብቸኝነቱ ፤ አላውቅም ። .................

እንደማልጠላት ብቻ እንጂ እንደማፈቅራት አታውቅም ፈፅሞ አታውቅም እኒም አልነገርኳትም። ጓደኝነቷን ላለማጣት ስል ብቻ ፣ ካጠገቧ እንዳታሸሸኝ ስል ብቻ ፣ እንዳትጠላኝ ስል ብቻ እውነት እውነቱን ትቼ ዋዛ ፈዛዛውን አወጋታለው ። በቀልዶቼ ደስ ይላታል .... ትስቃለሽ ፤ ሳቋን ሳይ ልቤ በደስታ ትቦርቃለች ።

እስኪ የዛን የሚስኪን ሰው ደብዳቤ ላንብብልሽ ............

የሚስኪኑ ሰው ደብዳቤ ቁጥር 144 .

ውዴ አንድ ምስኪን የመንግስት ደሞስተኛ ጥሬ ስጋን ከሚናፍቀው በላይ ትናፍቂኛለሽ ፤ ከእስፔ ሻል ክትፎ በላይ ውድ ሆነሽብኛል ፤ ከእንግዲህ ይቅር ብለሽኝ ከቤቴ እንደማትመለሺ አውቃለው ምክንያቱም ከደረጃዬ በላይ ሆነሽብኛል ፣ ከእንግዲህ አንቺ ማለት ለእኔ ኩንታል ጤፍ ማለት ነሽ። ክፉኛ የምመኝሽ ግን የማላገኝሽ ........ ውዴ አንቺ ማለት ለእኔ ጤፍ አለኝ ጎጃም በረንዳ ..... እንጀራዋንም አላይ አይነት ነገር ሆነሻል የእኔ ጤፍ ይቅርታ የእኔ ቆንጆ ትናፍቂኛለሽ ።

በሳግ ውስጥ ሆና ፈገግ አለችለትና ናቲ? ወዬ ..... ፍታኝ? ለምን አትፈታኝም እሺ አንድ እስቲክ ስጠኝ ? አልሰጥሽም ።

...... ናቲ ያለውበትን ጉድጓድ አንተ ትረዳኛለህ ብዬ አስቤ ነበር ግን አንተም ያው ነህ ከህቴ አትሻልም ያው ናቹ እሷም የመንደሩን ወሬ ፈርታ እንደዚህ ያሰረችኝ የዛች የሃሺሻም እህት እንዳትባል አይደል እንደዚህ ያሰረችኝ ....... ውጣልኝ !!!።

ለሚወዱት ሰው መዳኒት እንጂ መርዝ አይሰጥም ..... ግን መርዙ መዳኒት የሆነስ ጊዜስ ? እወዳታለው ስቃዩአን ማየት አልፈልግም ፤ ስለ ነገም አላውቅም ፣ ቢያንስ ዛሬን እፎይ ብላ ስትስቅ ማየት ልቤን ያደምቀዋል ........

(በጭስ ተደብቄ)

╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!