🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

'................ ፍቅር በዓይኑ ጥቅሻ በጠራችሁ ጊዜ መንገዶቹ ምን ያህል አስቸጋሪ እና | ቅኔ ያለው ትውልድ

"................ ፍቅር በዓይኑ ጥቅሻ በጠራችሁ ጊዜ መንገዶቹ ምን ያህል አስቸጋሪ እና አቀበት ቢሆኑም ተከተሉት...ክንፎቹ ሲያቅፏችሁም ተሸጎጡበት ። በላባዎቹ መሀል የተደበቁ ሰይፎች ቢያቆስሏችሁም ወደኋላ አታፈግፍጉ ..ሲያነጋግራችሁም እመኑት ። ድምፁ የሰሜን ኃይለኛ ንፋስ የአትክልትን ስፍራ እንደሚያወድም ሁሉ ህልሞቻችሁን ቢበታትንባችሁም እሱን ከማመን አታመንቱ........
ፍቅር ዘውድ የሚደፋላችሁን ያህል ይሰቅላችሁም ይሆናል ። የሚያሳድጋችሁንም ያህል ይከረክማችኋልም...እስከ ጫፍ ከፍ ብሎ በፀሃይ ውስጥ የሚወዛወዙትን እጅግ ለስላሳ ቅርንጫፎቻችሁን በፍቅር እንደሚደባብስ ሁሉ ፣ በመሬት ውስጥ ቁልቁል ወደ ስሮቻችሁ ወርዶም ተጠምጥሞ ከመሰረታቸው ይነቀንቃቸዋል
ፍቅር እነዚህን ሁሉ ነገሮች የሚያደርግባችሁ ፣ የልባችሁን ምስጢራት እንድታውቁ እና በዚያ ዕውቀትም የህይወት ልብ አንድ ግማድ እንድትሆኑ ነው.............
" የጥበብ መንገድ ፪ "
ካህሊል ጂብራን


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!