🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

'ቀን ያበደ ለታ' ተፈጥሮ በድንገት፣ዛብ በለቀቀበት፣ በዞረበት ጊዜ፣በዞረባት መሬት፣ ዶሮ ሲያንቀ | ቅኔ ያለው ትውልድ

"ቀን ያበደ ለታ"

ተፈጥሮ በድንገት፣ዛብ በለቀቀበት፣
በዞረበት ጊዜ፣በዞረባት መሬት፣
ዶሮ ሲያንቀላፋ፣በጓጉንቸር ጩኸት፣
በዘጠኝ ይነጋል፣ቀኑ ያበደ ለት፡፡
ጊዜ ቀስቱ ሲዝል፣ሲረግብ ደጋኑ፣
ቋጠሮው ሲላላ፣የተፈጥሮ ውሉ፣
ሳያልቅ ሌሊቱ፣እንደጭንጋፍ ሁሉ፣
በዘጠኝ ይነጋል፣እብድ ቀን ላመሉ፡፡
ጠብ-በመተቃቀፍ፣
ቁጣ-በፈገግታ፣
ፍቅር-በንክሻ፣
ሰላምታ-በቴስታ፣
ሀዘን-በዳንኪራ፣
ጋብቻ-በዋይታ፣
የሚሆነው ቀርቶ፣
የማይሆን ይሆናል፣ቀን ያበደ ለታ፡፡

{ጌትነት እንየው}


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!