🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

……………… 'ተረት . . ተረት 'በድሮ ጊዜ አንዲት ሴት ነበረች . . . ይቺ ሴት ልጅ | ቅኔ ያለው ትውልድ

………………

"ተረት . . ተረት


"በድሮ ጊዜ አንዲት ሴት ነበረች . . . ይቺ ሴት
ልጅ አልነበራትም . . ላልተሳለቹ ታቦት አልነበርም
ሆኖም ግን ልጆ ማግኘት አልቻለችም።

በመጨረሻ ለሴጣን ተሳለች ስለቷም ጋቢ ነበር። እናም እቺ ሴት ፀነሰች ፣ ወለድች ኃላም ስለቷን ለማድረስ ብፈልግም ሰይጣን የት እዳለ አታውቅምና ንሰሃ አባቷን ልጠይቅ ሄደች ። እሳቸውም እንዲህ አሏት፦

"በሁለት ሰዎቾ መሃከል ፀብ ተፈጥሮ አልታረቅም አሻፈረኝ ብሎ ለይቅርታና ለይቅር የሸሸ ሰው ስታገኚ ይህን ጋቢ አልብሽው እሱ ሰይጣን ነው" አሏት።

እሷም በሌላኛው ጊዜ ከአንድ ሸንጎ ቦታ ስታልፍ አንድ አልታረቅም ብሎ እምቢ ያለ ሰው አየች ሄዳም ጋቢውን አለበሰችው። ሰውየውም በብስጭት እንዴት ጋቢ ታለብሽኛለሽ ብሎ ተቆጣ
እሷም ንሰሃ አባቷ ያሏትን ነገረችው "እኔ ስለቴ ሞልቻለውም "አለችው።

እሱም ጋቢውን ጥሎ ተታርቆ ሄደ ይባላል።

ተረቴን መልሱ አፌን በዳቦ አብሱ።"

{የዛይ መሬት ከሚለው ፊልም ላይ የተወሰደ}


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!