🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ሙኒባ ማዛሪ በ18 ዓመቷ ነበር በቤተሰቧ አስገዳጀነት ትዳር የመሰረተችው።ትዳር በመሰረተች በሁለተኛ | ቅኔ ያለው ትውልድ



ሙኒባ ማዛሪ በ18 ዓመቷ ነበር በቤተሰቧ አስገዳጀነት ትዳር የመሰረተችው።ትዳር በመሰረተች በሁለተኛ ዓመቱ ከባለቤቷ ጋር ስትጓዝ የመኪና አደጋ ገጠማት ። በደረሰባት አደጋም የከፋ የጀርባ አጥንት ስብራትን ጨምሮ ውስብስብ የጤና እክል ገጠማት።

በተለያዩ ሆስፒታሎች ህክምና ቢደረግላትም ዳግም በእግሮቿ መራመድ ግን አልቻለችም። ይሄን በሰማች ጊዜም ለመቀበል ከበዳት።ይባስ ብሎ መውለድ እንደማትችል ሲነገራት ደግሞ የበለጠ ሃዘኗን ጨመረው ።ተስፋ
ቆረጠች።በርካታ የፈተና እና የመከራ ጊዚያትን በሆስፒታል ቆይታዋ አሳለፈች።

ነገር ግን መከራዋ እና ፈተናዋ አብሮት አልዘለቀም። ከለታት አንድ ቀን በጥዋት ተነስታ "ተስፋ መቁራጥ አማራጭ አይደለም !ተስፋ መቁራጥ ደስታን ነጣቂ ክፉ በሽታ ነው!" የሚለውን ደጋግማ ለራሷ ነገረች።ከዛም ፍርሃቷን አንድ በአንድ በመፃፍ አቃጠለችው።በሆስፒታሉ
ግድግዳ ተስፈዋን የሚያለመልም እና ከፍታዋን የተሸከሙ ስዕሎችን መሳል ጀመረች።

ሙኒባ የከፋ አደጋ በህይዎቷ አሰናክሏት የአካል ጉዳተኛ በመሆኗ "አበባዋ ረገፈ !" ሲሏት ተስፋ" ባለመቁረጥ ያሳየችው የመንፈስ ጥንካሬዋ ለስኬት አበቃት። ሙኒባ ከምትፈልገው እና
ከምታስበው በላይ ትልቅ ደረጃ፤ የላቀ ቦታ
ላይ ደርሰች። ተስፋ ሳትቆርጥ ባደረገችው ግስጋሴ ዛሬ ላይ ሙኒባ ማዛሪ በአለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሚባሉት እንስቶች
መካከል አንዷ ሆናለች።

የተባበሩት መንግስታት የመልካም ሰው ክቡር አንባሳደር ተብላ አለም በስኬት ክብር ከሚያወድሷቸው ጥቂት አንደበተ ርቱዕ ታዋቂ ሰዎች መካከል አንዷ ሙኒባ ሆናለች ።

አነቃቂ ንግግሮችን ለብዙ ሺዎች በማድረግ
የብዙዎችን ነፍስ ታለመልማለች እዲሁም
ድምፃዊ፣ሰዓሊ ስትሆን ፤ በጎ አድራጎቶችንም ታከናውናለች ።

ልጅ መወለድ ባትችልም እንኳን በማደጎ ልጅ አግኝታ ህይዎቷ ባጣችው የልጅ ፍቅር ታድሷል።
በሰው ልቦና ሊረሱ የማይችሉ ስራዎችንም እየሰራች ትገኛለች። በኑሮዋም ቅንጡ ሂወትንም
ትኖራለች።

መንገዷ ከባድ ቢሆንም መድረሻዋ ግን ስኬት ነው ምክንያቱም እሷ እንደምትለው ከመሞቷ
በፊት ስላልሞተች።

#ምንም ነገር ከማንችለው በላይ አልተሰጠንም!! መሆን የፈለግነውን ሁሉ መሆን ከፈለግን እንሆናለን!! እኛ በቃ እስካላልነው ድረስ የማያበቃ ስኬት እንገንባ !!


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!