Get Mystery Box with random crypto!

……………… ……………… እስኪ ስለ General theory of rela | ቅኔ ያለው ትውልድ

………………
………………

እስኪ ስለ General theory of relativity እናውራ።
ሁሉም ነገር አንፃራዊ እንደሆነ የሚያትተው ይህ መፅሐፍ የወጣው በ 1905 እ.ኤ.አ ነበር። በወቅቱ የጊዜን አንፃራዊነት አልበርት ሲያስረዳ " የጋለ ብረት ላይ ለአንድ ደቂቃ መቆም እና ከፍቅር ጓደኛህ ጋር አንድ ሰዓት ማሳለፍን ብታወዳድር የጋለ ብረት ላይ መቆም ረጅም ሆኖ ይሰማሃል" ይል ነበር ይባላል።

አልበርት አብዛኛውን የፊዚክስ ሃሳቦቹን የሚያመጣው በሚሰራቸው ሃሳባዊ ሙከራዎች (thought experiments) ነው። ከእነዚህ ሙከራዎች መካከል በ1905 እ.እ.አ የታተመው General theory of relativity ላይ ስለ ጊዜ (time dilation) የሰራው የሃሳብ ሙከራ (thought experiment) ለዛሬ እንመልከት።

እስኪ ሁለት ሰዎችን አስቡ፤ ሁለቱም ቁመቱ 1 ሜትር በመሆነ የመጓጓዣ አካል (መንኮራኩር) ውስጥ ናቸው እንበል።

የሁለቱም መንኮራኩር ጣራ ላይ መስታውት አለ፤ ሁለቱም የእጅ ባትሪ (ሌዘር) ይዘዋል።

በመቀጠል እነዚህ ሰዎች ወደ መስታውቱ ባትሪያቸውን አበሩ።

እንደሚጠበቀው ብርሃኑ መስታውቱ ላይ ተንፀባርቆ ይመለሳል። በዚህም ብርሃኑ ደርሶ መልስ 2 ሜትር ይጓዛል። ምስጋና ለ ጀምስ ማክስዌል ይሁን እና የብርሃን ፍጥነት ይታወቃል(300,000 ኪሜ በሰከንድ)።

ስለዚህ 2 ሜትሯን ለመጨረስ የሚፈጅበትን ጊዜ ማስላላት ይቻላል። በቀላሉ ርቀቱን ለብርሃን ፍጥነት በማካፈል ማወቅ ይቻላል።

t=2ሜትር÷300,000,000 ሜትርበሰከንድ= 6.6 ናኖሰከንድ

ይህ ሰዓት ለሁለቱም እኩል 6.6 ናኖ ሰከንድ ይሆናል።

ነገር ግን አንደኛው በፍጥነት ቢሄድ ( ለምሳሌ በብርሃን ፍጥነት ግማሽ) ቢጓዝ፤ ከቆመው መንኮራኩር ያለው ሰው የሚንቀሳቀሰው ውስጥ ያለውን ሰው ሲያይ፣ ብርሃን ከእጅ ባትሪው ተነስቶ 1 ሜትር ተጉዞ ጣራው ላይ ከመድረሱ በፊት 0.5 ሜትር ወደጎን ይጓዛል። በዚህም ምክንያት ቀጥ ብሎ ወደላይ ደርሶ መመለሱ ይቀርና ሰያፍ ይጓዛል።

ሰያፍ መሆኑ ደግሞ የሚጓዘውን ርቀን ይጨምረዋል። በትክክል ለማወቅ በፓይታጎረስ ቴረም ብንጠቀም

l=(x²+y²)½
x=ቁመት y=መንኮራኩሩ ወደ ጎን

የተጓዘው ርቀት
l=(1²+0.5²)½= 2.24ሜትር

ቅድም በተጠቀምነው መሰረት ጊዜን ብናሰላ፦
t=2.24ሜ÷300,000,000 ሜበሰከንድ
t=7.5 ናኖ ሰከንድ

ስለዚህ የቆመው ሰውየ የሚሄደውን ሰውን 7.5 ናኖ ሰከንድ እንደቆየ ያስባል፤ ይኸው የቆሞው ሰው የራሱን ሰዓት ግን 6.6 ናኖ ሰከንድ ነው ብሎ ያስባል።

ሰዎቹ መንታ ቢሆኑ እና በዚህ አይነት ሁኔታ ለ50 ዓመታት ቢቆዩ፤ አንዱ 50 ሌላኛው 56 ዓመት ከ10 ወር ይሆነዋል ማለት ነው (twin paradox).

ይሄን ሁሉ ላለማውራት መግቢያው ላይ ያለውን የፍቅረኛ እና የጋለ ብረት ላይ የመቆምን ተምሳሌት ይጠቀሙበታል።

ማጣቀሻ
¹ Concepts of modern physics Arthur Beiser et al
² Relativity : the special and the general theory Albert Einstein
³ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Time_dilation
https://steemit.com/physics/@procrastilearner/intuitive-special-relativity-time-dilation


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!