🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

……………'በዘመናችን ብሄርተኝነት ማለት ሳይደክሙ የሌሎችን የድካም ውጤት መቀማት መሆኑን አውቃለው። | ቅኔ ያለው ትውልድ

……………"በዘመናችን ብሄርተኝነት ማለት ሳይደክሙ የሌሎችን የድካም ውጤት መቀማት መሆኑን አውቃለው። አንድ ሰው በግሉ ስኬት መቀዳጀት ሲያቅተው በጥረታቸው ብልጫ ያስመዘገቡ ግለሰቦችን ስኬት ወደ ብሔር ስኬት ለውጦ ባዶነቱን ለመሙላት ይሞክራል። ሌላው እልም ያለ ፈሪ ሆኖ ሳለ "የበላይ ዘር" እያለ ይፎክራል። ብብቱ ውስጥ ገብተው ካልደገፉት በቀር አልጋ ላይ መውጣት የማይችል ሰውዬ፤ አበበ ቢቂላ በተነሳ ቁጥር "አበበ ኬኛ" እያለ ይኩራራል። በላይና አበበ ይስመዘገቡት ድል በላብና በደም የተገኘ የግለሰብ ጥረት ውጤት ነው። ድል በዘር አይተላለፍም የአባቶች ታላላቅነት በዘር ወደ ልጆች የሚተላለፍ ቢሆን ኖሮ ግሪኮች በዛሪይቱ የአውሮፓ እግር ሥር እንደ ጉድፍ ወድቀው ባልተገኙ ነበር። ብሔርተኝነት የግለሰብ ጥረትን ሰርቆ የራስን ድክመት ለመሙላት የሚደረግ መሰሪ እንቅስቃሴ ነው።…"

{…"ከአሜን ባሻገር" . . .በእውቀቱ ስዩም }


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!