🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

' #ብቸኛ_ልጄን_ከሞት_ታደጉልኝ ' #እናት ህፃኗ #ከአቅሟ_በላይ የሆነ ጭንቀት ተሸክማለች | ቅኔ ያለው ትውልድ

" #ብቸኛ_ልጄን_ከሞት_ታደጉልኝ " #እናት
ህፃኗ #ከአቅሟ_በላይ የሆነ ጭንቀት ተሸክማለች

ይህች አንጀት የምትበላ ህፃን #ብሌን_ሙሉጌታ ትባላለች!ከተወለደች ጀምሮ ሁለት አመት ከስድስት ወር ህመሟሳይታወቅላት ስትሰቃይ ቆይታ በአንደኛው ቀን እናት ልጇን አቅፋ መንገድ ላይ ያያት ልበደግ ዶክተር የጥፍሯ መበለዝ፣የእጇንና ደምስሯ በተለየ ሁኔታ መጥቆር በልብ ኬዝ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተጠራጥሮ ምንም አቅም የሌላቸውን እናትና ልጅ ወደ ራሱ ክሊኒክ ወስዶ ለምስኪኗ ህፃን ብሌኔ ሙሉ ምርመራ በነፃ አደረገላት!!

ዶ/ር አብዱ እንደገመተው የምታሳሳው ብሌኔ የልብ
ክፍተት እንዳለባትና በተፈጥሮም የስር መተላለፍና ከልቧ ወደ ሳንባዋ ደም የሚያስተላልፍ ጥበት ስላለባት ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ይልካቸዋል!!

እናት ተደናግጣ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተጣድፋ ብትሄድም ብቸኛ ልጇ ከባድ ሁኔታ ላይ እንዳለችና ከሌሎቹ ህፃናት በተለየ ተደራራቢ የልብ ህምም እንዳለባት በድጋሚ ይነግሯታል!!ህክምናውም ሀገር ውስጥ እንደማይቻልና የሚረዳሽ ካገኘሽ እስራኤል በቶሎ ወስደሽ ልጅሽን ማዳን ትችያለሽ ብለዋታል

ኑሮዋ ከእጅ ወደ አፍ ለሆነባት እናት ወደ አምላኳ ከመፀለይ በቀር ልጇን ወደ ውጪ ወስዳ የማሳከም
ምንም አቅም የላትም!"የብቸኛ ልጄ የሞቷን ቀን ከምጠብቅ እባካችሁን አድኑልኝ "ብላ በእንባ እየተማፀነቻችሁ ነው!! እህታችን ብሌንም ድካሙ እንደ እኩዮቿ መራመድ እንዳትችል አድርጓታልና#እንድረስላቸው

ምንም ማድረግ ባንችል #እየፀለይን #ሼር_SHARE
በማድረግ እናግዛቸው
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
#አካውንት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000167198817-ፅጌ ጋዲሳ
#ስልክ
0983750882-ፅጌ ጋዲሳ
0910214887-ሙሉጌታ አበራ
"ባይሽ ኮልፌ በጎ አድራጎት"