Get Mystery Box with random crypto!

ነፃ የትምህርት እድል (Scholarship) መረጃ ለተማሪዎች ክፍል-1 በ bliss_scholars | የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር

ነፃ የትምህርት እድል (Scholarship) መረጃ ለተማሪዎች ክፍል-1

በ bliss_scholarship ተዘጋጅቶ በ ኢትዮ Students የቀረበ

Scholarship ምንድነው?

Scholarship ማለት ለአንድ ተማሪ የሚሰጥ የትምህርት ወጪን በከፊል ወይም በሙሉ መሸፈን የሚያስችል ሽልማት ወይንም እርዳታ ነው::

የተለያዪ ሀገራትም ይህንን በመስጠትም ይታወቃሉ ከነዚህም መካከል አሜሪካ ለብዙ ተማሪዎች ይህንን እድል በመስጠት ቀዳሚ ሀገር ናት::

Scholarship ማግኘት ምን ይጠቅመኛል?

ግልፅ ከሆነው እና ዋነኛ ጥቅም ስንጀምር የትምህርት ወጪ በሙሉ ወይም በከፊል ተሸፍኖ እንዲሁም እጅጉን የተመቻቸ እና ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ማግኘት ያስችላል::

ሌላው ጥቅም ደግሞ ሰፊ የሆነ የስራ እድልን ይፈጥራል:: በነዚህ ሀገራት አንድ ተማሪ ጠንክሮ እስከተማረ ድረስ በሚመረቅበት ጊዜ እጁን ስመው የሚቀጥሩት ብዙ ኢንተርናሽናል እና የሀገር ውስጥ ድርጅቶች አሉ::

ከላይ ከተጠቀሱት ጥቅሞች ባለፈ Traveling Experience ወይም አንድ ተማሪ ወደ ውጪ ሀገር በሚሄድበት ጊዜ በዚያ የሚያገኘው ልምድ: እንዲሁም ከተለያዪ ሀገራት የሚመጡ ሰዎችን: አዲስ ባህል: አዲስ አስተሳሰብን በመማር የሚገኘው ጥቅም ከምንም በላይ ነው:: ይህም ሁሉ ሲደመር highly skilled, matured, and independent የሆነ ማንነት እንዲኖረን ያስችላል::

በ2019/20 የትምህርት ዘመን በአሜሪካ በተደረገ ጥናት በአንድ አመት ውስጥ ብቻ ከ1 ሚልዮን በላይ የሌላ ሀገር ተማሪዎችን አሜሪካ ያስተናግደች ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 50% የሚሆኑት ከቻይና እና ህንድ የመጡ ናቸዉ::

ቻይና እና ህንድ ኢኮኖሚያቸው በፍጥነት የማደጉ አንዱ ሚስጥር ካደረጉት ሀገራት የሚወስዱት ልምድ ነው:: ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችም እጅግ በጣም ጥቂት እንደነበሩ ጥናቱ ያሳያል:: የብዙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ችግር በቂ መረጃ አለመኖር ነው::

በቀጣይ ክፍል የአብዛኛው ተማሪ ጥያቄ የሆነውን:
- እንዴት መሞከር እችላለሁ?
- ምን ያስፈልገኛል ?
- ከየት ልጀምር?
- ምን አይነት እድሎች አሉ?
- የትኞቹ ሀገራት የተሻለ አማራጭ አላቸው?
- Agent ምናምን ብለው ብር ሚቀፍሉት በእርግጥ Agent ያስፈልጋል ??
- እንዲሁም የWebsite ጥቆማ መልስ ይኖረናል::

ይህን መረጃ ያካፈለንን bliss_scholarship ከልብ እናመሰግናለን በ ክፍል 2 ሌሎች መረጃዎችን ይዘን እንቀርባለን

bliss_scholarship ን ማግኘት ለምትፈልጉ ከታች ባለው Link ተቀላቀሏቸው
@bliss_scholarship
@bliss_scholarship


ሼር ማድረግ አትርሱ
https://t.me/joinchat/AAAAAFjmHytEWWbWoq3PAQ
@Ethio_Students