🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ማስታወቂያ የ2015 ት/ት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ 1/የ2015 ት/ት | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

ማስታወቂያ
የ2015 ት/ት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ

1/የ2015 ት/ት ዘመን ፈተና ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 20/2015 ዓ/ም ድረስ ብቻ ይካሄዳል።
2/ ማንኛውም የስም፣ የፆታ፣ የተፈጥሮ/የማህበራዊ ዘርፍ እና የፎቶ ማስተካከያ ከፈተና በፊት ስለማይደረግ እያንዳንዱ ተፈታኝና እና መዝጋቢ ትክክለኛነቱን የማጣራትና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። ምክንያቱም ምዝገባው በበየነ መረብ በመሆኑ በትምህርት ቤት ደረጃ የተካሄደው የምዝገባ መረጃ በቀጥታ በማንም ሳይነካ ወደ ተቋማችን የመረጃ ቋት የሚገባ በመሆኑ ነው።
3/ከሚያዚያ 20/2015 ዓ/ም በኋላ በግለሰብ ወይም በተቋም በኩል የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ በጥብቅ እናሳስባለን።
4/ፈተናው የምሰጠው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሲሆን የመፈተኛ ጊዜን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ የምንገልጽ ይሆናል። እስካሁን የመፈተኛ ጊዜ አልተገለጸም።

ስለሆነም ተፈታኞች ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ እያሳሰብን መልካም ውጤት እንዲያስመዘግቡ እንመኛለን።

የፈተና ኩረጃና ስርቆትን በጋራ እንከላከል!!

የት/ት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot