Get Mystery Box with random crypto!

ዕድሜያቸው 18 ዓመት የሞላቸውና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ወታደራዊ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

ዕድሜያቸው 18 ዓመት የሞላቸውና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ለሁለት ዓመት ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደውን አዲስ አዋጅ ፀደቀ

የተወካዮች ምክር ቤት የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት አዋጅ አፀደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕድሜያቸው 18 ዓመት የሞላቸውና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ለሁለት ዓመት ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደውን አዲስ አዋጅ አፀደቀ፡፡

ምክር ቤቱ ከትናንት በስቲያ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፣ መንግስት አዘጋጅቶ ያቀረበውን የተሻሻለ የመከላከያ ሰራዊት ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጪ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ዲማ ኖህ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ተማሪዎች በፈቃዳቸው በመደበኛ መከላከያ ሰራዊት ወይም የብሔራዊ ተጠባባቂ ሃይል አባል የሚሆኑ ከሆነ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ተያያዥ መብቶችንና ጥቅሞች እንዲጠብቁላቸው ያደርጋል ብለዋል፡፡

በመንግስት ተዘጋጅቶ የቀረበው የተሻሻለ የመከላከያ ሰራዊት ረቂቅ አዋጅ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ሆኖ የተጣለበትን ሀገርን የመጠበቅ ተልክኮ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመወጣት እንዲችል ያደርገዋል ተብሏል፡፡

በመንግስት የተሻሻለውና ከትናንት በስቲያ በምክር ቤቱ የፀደቀው ይህው አዋጅ የሰራዊቱ አባላት የጡረታ መውጫ የእድሜ ጣሪያ አወሳሰን እንዲሁም የአገር ህልውና ከባድ አደጋ ላይ በሚወድቅ ጊዜ ከሰራዊቱ የተገለሉ አባላት መቀጠር የሚችሉበትን ሁኔታ ሁሉ አካቶ መያዙም ተገልጿል፡፡

አዲስ አድማስ


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT