Get Mystery Box with random crypto!

የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮችን ሊያስተናግድ ነው:: የኢትዮጵያ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮችን ሊያስተናግድ ነው::

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ተወካዮች በቀጣይ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን ከ22ኛው ሳምንት ጀምሮ የሚያስተናግደውን የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ለአራተኛና ለመጨረሻ ጊዜ ዛሬ ረፋድ ላይ ተመልክተዋል።

ቀደም ባሉ ምልከታዎቻቸው የሊጉ የበላይ አካል በሜዳውና ከሜዳው ውጪ ያሉ መሻሻል የሚገባቸውን ጉዳዮች ባስቀመጠው መመሪያ መሠረት ተፈፃሚ መሆናቸውን ተዟዙሮ ከተመለከተ በኋላ ሊጉ በቀጣይ ሀዋሳ ላይ እንደሚደረግ ማረጋገጫ ሰጥቷል። በዚህም መሠረት ፕሪምየር ሊጉ የ22ኛ ሳምንት ጨዋታውን በአዳማ ከጀመረ በኋላ ከመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎች ጀምሮ እስከ 27ኛው ሳምንት ድረስ ሀዋሳ የሊጉን ውድድር ታስተናግዳለች::

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot