Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርት ሚኒስቴር የእንግሊዝኛ ቋንቋን በበጎ ፍቃደኝነት የማስተማር ፍላጎት ያላቸው ዜጎች የሚመዘ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

የትምህርት ሚኒስቴር የእንግሊዝኛ ቋንቋን በበጎ ፍቃደኝነት የማስተማር ፍላጎት ያላቸው ዜጎች የሚመዘገቡበት የመረጃ ፖርታል ይፋ አድርጓል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት የመረጃ ፖርታሉ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት የሚታየውን የጥራት ጉድለት ለማስተካከል እንደሚያግዝ ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

በእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት የጥራት ውስንነትን ለማስተካከል በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እንዲሰጡም ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ነጻ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መማሪያ መተግበሪያ ማዘጋጀቱንም ሚኒስትሩ አስታውሰዋል።

በተጨማሪም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን እና ተመራማሪዎች በተቀናጀ መልኩ ግንኙነት የሚያደርጉበት ፖርታል ሥራ መጀመሩንም የኢዜአ ዘገባ ያሳያል፡፡

የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት በኢትዮጵያ ከ70 አመት በላይ የማስተማሪያ ቋንቋ በመሆን እያገለገለ ይገኛል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot