Get Mystery Box with random crypto!

#Tigray በትግራይ ተቋርጦ የነበረው መደበኛ ትምህርት ከሠኞ ጀምሮ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

#Tigray

በትግራይ ተቋርጦ የነበረው መደበኛ ትምህርት ከሠኞ ጀምሮ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተጀምሯል።

ትምህርት የተጀመረው አዳዲስ አሰራሮችን  ተግባራዊ በማድረግ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ ለኢቢሲ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ  ምን አሉ ?

" ትምህርቱ ከሚያዚያ 24 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 7 ቀን 2015 ድረስ ለ2 ወር ተኩል በማካሄድ  የመጀመሪያው መንፈቅ ይጠናቀቃል። ይህም እንደ አንድ ወሰነ ትምህርት ጊዜ ይይዛል።

እንዲህ ያለው የትምህርት ዘዴ ወይም (Accerated Learning Program) ተማሪዎች እድሜያቸው መድረስ በሚገባቸው የትምህርት እርከን ላይ እስኪደርሱ በዓመት ሁለት ደረጃ ትምህርቶችን እንዲያልፉ ተደርጎ ተሰርቷል።

በዚህም አንድ ዓመት 4 የወሰነ ትምህርት ጊዜ በማድረግ ሁለት ደረጃ ትምህርት በአንድ ዓመት እንዲጨርሱ ይደረጋል። "

በሌላ በኩል ቢሮው ፥ በጦርነቱ ምክንያት ብዙ ጉዳት በመድረሱ የልዩ ፍላጎት የሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ቁጥራቸው  በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨምር አሳውቋል።

የጉዳቱን መጠን በመረዳት የፌዴራል መንግስት፣ ትምህርት ሚኒስቴር ፣ ዓለም አቀፍ  የእርዳታ ድርጅቶች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ ድጋፍ  እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot