Get Mystery Box with random crypto!

በስልጤ ዞን የትምህርት ማስረጃን የማጣራት ስራ መጀመሩን ተከትሎ 67 መምህራን ስራ ጥለው ጠፉ በ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

በስልጤ ዞን የትምህርት ማስረጃን የማጣራት ስራ መጀመሩን ተከትሎ 67 መምህራን ስራ ጥለው ጠፉ

በስልጤ ዞን የትምህርት ማስረጃን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የማጣራት ስራ ተጀምሮ ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልኮ ፍተሻ ተደርጓል። ይህንኑ ተከትሎ የትምህርት ማስረጃቸው ሀሰተኛ ሆኖ የተገኘባቸው የተወሰኑ መምህራን በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 67 መምህራን ስራ ጥለው መጥፋታቸው ተነግሯል ።

በተያዘው በጀት ዓመት ከጥቅምት ወር ጀምሮ 4ሺ 4 መቶ 74 የትምህርት ማስረጃዎች ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልከው በተደረገ የማጣራት ስራ የ82 መምህራን ሀሰተኛ ሆኖ መገኘቱን የስልጤ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ  አ/ቶ ሽኩራል አወል ከብስራት ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል ። ከነዚህ መምህራን መካከል 28 ቱ በቁጥጥር ስር ሲውሉ ቀሪዎቹ መጥፋታቸው ተገልጿል ። 

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል በ15 መምህራን ላይ የፍርድ ውሳኔ የተላለፈ ሲሆን ቀሪ መምህራን በገንዘብ ዋስ ከወጡ በኋላ መጥፋታቸውን አክለዋል። የ67ቱ መምህራን ስራቸውን ጥለው መጥፋት በአንድ ወረዳ ብቻ የ23 መምህራን የትምህርት ማስረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ ማረጋገጥ ተችሏል ።

ሀሰተኛ ማስረጃው በተራቀቀ መንገድ የተሰራ መሆኑንና በምርመራ ወቅት ማወቅ እንደተቻለው ደላሎችን ጨምሮ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በዚሁ ተግባር ተሳትፎ ያላቸው ሰዎች እንዳሉ መምህራኑ ተናግረዋል ።

እንዲህ ዓይነት ችግሮች ዳግመኛ እንዳይከሰቱና ለመከላከል እንዲቻል የሚመለከተው አካል ሁሉ በጉዳዩ ዙሪያ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አ/ቶ ሽኩራል ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot