🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

#ሪሜዲያል #UPDATE ትምህርት ሚኒስቴር ትላንት ሰኞ ምሽት ከፕሬዚደንቶችና የተቋማት ሃላፊዎች | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

#ሪሜዲያል #UPDATE

ትምህርት ሚኒስቴር ትላንት ሰኞ ምሽት ከፕሬዚደንቶችና የተቋማት ሃላፊዎች ጋር ከተወያየ በኃላ የሬሜዲያል ፈተና አሰጣጥ በሚከተለው መልኩ እንዲከናወን ወስኗል።

በ26/10/2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕርግራም ፈተናዎች #ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ እንዲደረግ ተወስኗል።

ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ #ካምፓስ ያላቸውን #የግል_ከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማት ፈተና  ወደ ፊት ቀርቦ በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም  እንዲሰጥ እንዲደረግ።

በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች ፈተና መስጠቱን ወደ መስከረም ወር ማስተላለፉ በተማሪዎችና በተቋማት ላይ የሚያሳድረውን ጫና ከግምት በማስገባት የተዘጋጁትን ፈተናዎች በመለወጥ ፈተናዎች ኢንክሪፕትድ ሆነው ለዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቶች ደርሰው እንዲባዙና ሁሉም ፈተናዎች በተመሳሳይ ጊዜ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ እንዲሰጡ እንዲደረግ።

የፈተና ጥያቄዎች ለዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቶች ከመድሳቸው በፊት ተማሪዎች #ከቀኑ_6 ሰዓት ላይ ተፈትሸው ወደ መፈተኛ አዳራሽ ገብተው ፈተናውን እንዲጠባበቁ በማድረግ እንዲፈፀም ውሳኔ ተላልፏል።

ተቋማት ከትምህርት ሚኒስቴር በተላከላቸው ውሳኔ መሰረት ተማሪዎቻቸው #ከቀኑ_6 ሰዓት ተፈትሸው ወደመፈተኛ ክፍል ገብተው ፈተናውን እንዲጠባበቁ።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot