🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና መውሰጃ የይለፍ ቃል እና መግቢያ አልተሰጠንም በሚል ተማሪዎች ቅሬ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና መውሰጃ የይለፍ ቃል እና መግቢያ አልተሰጠንም በሚል ተማሪዎች ቅሬታ ሲያቀርቡ ነበር። ይህን ተከትሎም የዪኒቨርሲቲውን ተማሪዎች ኅብረት ተወካይ አነጋግረን የነበረ ሲሆን ዛሬ ውይይት እንደሚኖር እና መፍትሔ እንደሚሰጥ አሳውቀውን ነበር።

በዚህም መሠረት ይህንን መልዕክት ዩኒቨርሲቲው አስተላልፏል።

ለ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና username እና password ያልመጣላችሁ ተማሪዎች በሙሉ

በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2015 ዓ.ም ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና የመግቢያና የምስጢር ቁጥር (username and password) ያልመጣላችሁ ተማሪዎች ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰአት ላይ ሬጅስትራር ቢሮ ድረስ በመምጣት እንድትወስዱ እናሳስባለን።

የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትሬሽንና ፕሮግራሚንግ ም/ፕሬዝዳንት

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT