Get Mystery Box with random crypto!

የሚያጠቡ ተፈታኞች ሞግዚት ይዘው እንዲገቡ ተፈቀደ አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

የሚያጠቡ ተፈታኞች ሞግዚት ይዘው እንዲገቡ ተፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ የሚያጠቡ ተፈታኞች አንድ ሴት ሞግዚት ይዘው እንዲገቡ መፈቀዱን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

መውለጃ ወራቸው የደረሰ ነፍሰ ጡር እና ጡት የሚያጠቡ ተፈታኞች በሚቀጥለው ዓመት ተዘጋጅተው እንደ መደበኛ ተፈታኝ ቢፈተኑ እንደሚመከር አገልግሎቱ አስገንዝቧል፡፡

ይሁን እንጅ ለመፈተን የወሰኑ ከሆነ÷ ጡት የሚያጠቡት ተፈታኞች አንድ ሴት ሞግዚት ይዘው በመግባት እንዲፈተኑ ተገቢው ድጋፍ ይደረግላቸዋል መባሉን የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

የተፈታኞች መብትና ግዴታ እንዲሁም የተከለከሉ ነገሮች በተመለከተም÷ በተፈታኟና በሞግዚቷ ላይ ተግባራዊ እንደሚደረጉ ነው አገልግሎቱ ያሳሰበው፡

Fana Broadcasting corporate

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT