Get Mystery Box with random crypto!

አዲግራት ዩኒቨርስቲ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን 832 አዲስ ተማሪዎች መቀበሉን አስታወቀ። | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

አዲግራት ዩኒቨርስቲ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን 832 አዲስ ተማሪዎች መቀበሉን አስታወቀ።

ዩኒቨርስቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ1 ሺሕ 500 በላይ ተማሪዎች ታህሳስ 6 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚያስመረቅም ተመላክቷል።

የዩኒቨርስቲው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ዮሐንስ ከበደ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹን የተቀበለው የመመገቢያ፣ የመማሪያ፣ የመኝታ እና ሌሎች ለመማር ማስተማር ሥራው አስፈላጊ የሆኑ የዝግጅት ሥራዎችን ካጠናቀቀ በኋላ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የዩኒቨርስቲውን ቅጥር ግቢ በማስዋብና በማፅዳት ተማሪዎቹን መቀበሉን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ዩኒቨርስቲው ትምህርታቸውን በተለያዩ ምክንያቶች አቋርጠው ከነበሩ ከ5 ሺሕ በላይ ተማሪዎች መካከል ዳግም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ 1 ሺሕ 500 ተማሪዎችን የፊታችን ቅዳሜ እንደሚያስመርቅም ዮሐንስ አመልክተዋል።

የመቀሌ እና የአክሱም ዩኒቨርስቲዎች በተያዘው የትምህርት ዘመን የሚያስተምሯቸውን ከ2 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ባለፈው ሳምንት መቀበላቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot