Get Mystery Box with random crypto!

የእርዳታ ተማጽኖ ዲያቆን ሱራፌል ገረመው መኮንን የ24 ዓመት ወጣት ሲሆን፤ የግራፊክስ ባለሙያ ነ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

የእርዳታ ተማጽኖ

ዲያቆን ሱራፌል ገረመው መኮንን የ24 ዓመት ወጣት ሲሆን፤ የግራፊክስ ባለሙያ ነው።

እንዲሁም በረጲ መካነ ጎልጎታ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በድቁና አገልጋይ ነው።

ባለፉት ስድስት ወራት በገጠመው ከባድ የጉበት ህመም ምክንያት በተለያዩ ሆስፒታሎች የህክምና ክትትል ሲያደርግ ቢቆይም፤ ህመሙ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ አስቸኳይ የጉበት ንቅለ ተከላ ማድረግ እንደሚገባው የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ቦርድ ወስኗል።

የጉበት ንቅለ ተከላ ህክምናው በሀገር ውስጥ የማይሰጥ ሲሆን፤ በውጭ ሀገር ህክምናውን ለማግኘት እስከ ስድስት ሚሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ተጠይቋል።

ይህ ወጪ ከቤተሰብ አቅም በላይ በመሆኑ የወገኖቻችንን ድጋፍ መጠየቅ ግድ ብሎናል።

በመሆኑም በወጣት ሱራፌል ገረመው የህክምና ድጋፍ አስተባባሪዎች፤ መሰረት ፀጋዬ፣ አለልኝ ዋለ እና ሎንያስ ገዛኸኝ ስም በጋራ በተከፈቱ አካውንቶች፤

1000610015585 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
2957769765811 ዳሸን ባንክ
177682853 አቢሲኒያ ባንክ

የተቻላችሁን ወገናዊ ድጋፍ እንድታደርጉልን እንጠይቃለን።

ለተጨማሪ መረጃ
+251947328673 ኤልሳቤጥ ገረመው
+251946727171 ሎንያስ ገዛኸኝ