Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የፃፈው ደብዳቤ ፡ ጉዳዩ፦ ያለአግባብ ገንዘብ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የፃፈው ደብዳቤ ፡


ጉዳዩ፦ ያለአግባብ ገንዘብ ከባንክ ወጭ ያደረጉ ተማሪዎችን ይመለከታል፤

እንደሚታወቀው ባንካችን መጋቢት 06/2016ዓ.ም የሲስተም ማዘመን ስራ እየተሰራ በተፈጠረው የሲስተም ችግር ምክንያት ደንበኞች ያለአግባብ ገንዘብ ሳይኖራቸው ከሂሳባቸው ወጭ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት ባንካችን ከአ/ምንጭ ዩኒቨርስቲ ጋር በትብብር በተሰራው የማስመለስ ስራ አብዛኛው ደንበኞች ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ መመለስ ችለዋል፡፡ ነገር ግን ጥቂት የሚባሉ ደንበኞች ዕዳቸውን ከፍለው በሚፈለገው ፍጥነት ሊመልሱ አልቻሉም፡፤

በመሆኑም ዩኒቨርስቲው ይህንን የሀገር ሃብት ለማስመለስ እስካሁን ድረስ ለሠራው ሥራ ምስጋናችንን እያቀረብን፣ የቀረውን ገንዘብ ማስመለስ ይቻል ዘንድ ከዚህ ደብዳቤ ጋር ባያያዝነው ሠንጠረዥ ላይ በተመለከተው ዝርዝር መሠረት ልክ እንደዚህ ቀደሙ በተቋሙ ለሚገኙ ተማሪዎች ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ #በ48 ሰዓት ጊዜ ውስጥ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተመላሽ እንዲደረግ ልዩ የሆነ መመሪያ እንዲሰጣቸው በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

[የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ]

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT