🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በኦሮሚያ ክልል ተቀስቅሶ በነበረው ሁከት ሳቢያ ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው ለነበሩና በተለያዩ ምክንያ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

በኦሮሚያ ክልል ተቀስቅሶ በነበረው ሁከት ሳቢያ ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው ለነበሩና በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት ቤት ውጪ ለሆኑ ሕፃናት የአስቸኳይ ጊዜ የተከታታይ ዓመት ትምህርት መርኃግብር ይፋ ሆነ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር፣ የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ)፣ ጄኔቫ ግሎባል እና ኢጁኬሽን ካንኖት ዌት ይፋ ያደረጉት ፕሮግራም፣ በምሥራቅ ሐረርጌ አራት ዞንና በምሥራቅ ወለጋ ዞን አንድ ወረዳ ውስጥ ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተሰምቷል፡፡

ኤጁኬሽን ካንኖት ዌይት የተባለው ተቋም ለመርኃግብሩ ማስጀመሪያ 82 ነጥብ 14 ሚሊዮን ብር፣ እንዲሁም ጄኔቫ ግሎቫል 6 ሚሊዮን ብር እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች 14 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በመመደብ በዓመት 8 ሺ 274 ሕፃናትን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ እየሠሩ መሆናቸውንም ተሰምቷል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በነበረው ሁከት ምክንያት ከትምህርት ገበታ የተፈናቀሉ ሕፃናትና ቀደም ሲል በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከትምህርት ቤት ውጪ የነበሩ እድሜቸው ከ9 እስከ 14 የሆናቸው ሕጻናት ያባከኑትን የትምህርት ጊዜ በተፋጠነ የትምህርት አሰጣጥ መርኃግብር በመደገፍ ከዕድሜ አቻዎቻቸው ጋር በክፍል እንዲስተካከሉ ማድረግ የመርኃግብሩ ዓላማ ነው ተብሏል፡፡

አካል ጉዳተኛ እና ሴት ሕጻናትን በበለጠ ይጠቅማል በተባለው የአስቸኳይ ጊዜ የትምህርት መርኃግብር በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከ30 ሺህ የሚበልጡ ሕፃናትን በትምህርት፣ እንዲሁም ከ30 ሺ የሚበልጡ እናቶቻቸውን ደግሞ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡

በግጭቱ ምክንያት ከምሥራቅ ሐረርጌና ከኦሮሚያ ዞኖች ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው የነበሩና ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ ሕፃናት የአስቸኳይ ትምህርቱን ከጀኔቫ ግሎባልና ከኢጁኬሽን ካንኖት ዌት ጋር በመተባበር ተግባራዊ የሚያደርጉ አምስት ግብረሰናይ ድርጅቶች በውድድር መመረጣቸውንም የጄኔቫ ግሎባል ዓለምአቀፍ ተቋም የኢትዮጵያ ቢሮ ዳይሬክተር ሳሙኤል አስናቀ ሲናገሩ ተሰምቷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ በ2018 ሰራሁ ባለው ጥናቱ መሠረት ዕድሜአቸው ለትምህርት የደረሱና ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ሲገባቸው ከትምህርት ቤት ውጪ የሆኑ ሕፃናት ቁጥር በኢትዮጵያ ከ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ነው ብሏል፡፡

[Sheger FM]


#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT