Get Mystery Box with random crypto!

60 ከፍተኛ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች አመራርነት እና አገልጋይነትን በተግባር ሊሰለጥኑ መሆኑ ተገለጸ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

60 ከፍተኛ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች አመራርነት እና አገልጋይነትን በተግባር ሊሰለጥኑ መሆኑ ተገለጸ!

ከሁሉም ክልሎች በከፍተኛ ውጤት ያጠናቀቁ 60 ተማሪዎች አመራርነትን እና አገልጋይነትን በተለያዩ ተቋማት ተሰማርተው በተግባር እንደሚሰለጥኑ የሴቶች፣ ሕፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ ገለጹ።

ለዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ወጣቶቹን ከሚያሰለጥነው 'ሴንተር ፎር አፍሪካን ሊደርሺፕ' ከተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር ተፈራርሟል ብለዋል።

ወጣቶቹ 6 ሺህ ብር ወርሃዊ ደመወዝ ይከፈላቸዋል ተብሏል።

ፕሮግራሙ ለተከታታይ አምስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን በየዓመቱ የወጣቶቹ ቁጥር እየጨመረ እንደሚሄድ ወ/ሮ ፊልሰን ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

Via EBC

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT