Get Mystery Box with random crypto!

የተማሪዎች መልዕክት ለ #MoSHE ሰላም እንዴት ናችሁ የዘወትር የፔጃችሁ ተከታታይ ነኝ መል | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

የተማሪዎች መልዕክት ለ #MoSHE

ሰላም እንዴት ናችሁ የዘወትር የፔጃችሁ ተከታታይ ነኝ

መልዕክት ለማስተላለፍ ነበር ......

እንደሚታወቀው የአዲግራትና አክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርት ካቆሙ ይኸው ድፍን አንድ ዓመት ሊሞላቸው በጣም ጥቂት ቀናቶች ብቻ ነው የሚቀራቸው ። አስቡት እስቲ በሌላ ዩኒቨርስቲ ያሉ ጓደኞቻቸው ሲማሩ ማየትና እነሱ ደግሞ ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ሲመለከቱ ምን ያህል የስነ ልቦና ጫና እንደሚደርስባቸው ማንም የሚረዳው ነው። እነዚ ተማሪዎች አጓጉል ነው የሆኑት ። ነገ ዛሬ እንጠራለን በሚል ተስፋ በመጠባበቅ ላይ ናቸው ።በሌላ በኩል ብንጠራስ በእርግጥ በሰላም, ሰላማችንና ደህንነታችን ተጠብቆ እንማራለን ወይ በሚል ስጋት ጭንቅ ላይ ናቸው ። ምክንያቱም የምናየውና የምንሰማው ማለት በቦታው ካሉ ቤተሰቦቻችንና ወገኖቻችን የሚሰጡን መረጃ እንኳን የከፍተኛ ትምህርት (ዩኒቨርስቲ ) ለማስጀመር ይቅርና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለማስጀመር እጅግ አዳጋች ሁኔታ ነው ያለው። ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ በሚቻል ሁኔታ መሠረተ ልማቶች ወድመዋል ። ውሃ፣ መብራት ፣ስልክ ፣ህክምና ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው። ኢንተርኔትማ የቅንጦት ነው አይታሰብም። በተለይ እነዚህ ሁለቱ ዩኒቨርስቲዎች (አክሱምና አዲግራት) በጦርነቱ ወድሟል የተረፈው ንብረት ተዘርፏል። ለምን ግልጽ አላደርገውም ዩኒቨርስቲነቱ ቀርቶ የኤርትራ ና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የጦር ካምፖ ሆኗል ።ጦርነቱም እንደቀጠለ ነው።እውነታው ይሄ ሆኖ ሳለ መንግስት በቅርብ ቀን ሁሉን ነገር አስተካክዬና አሟልቼ ተማሪዎቼን እጠራለው የሚለው ነገር ተማሪዎችን ተስፋ ከመስጠት ውጪ እውነታውን አያንፀባርቅም ። በተማሪዎቹ ስነልቦና ላይ መጫወትም ነው።ከተሞቹ መሰረተልማት ሳያገኙ ለዩኒቨርስቲዎቹ ብቻ ተነጥሎ የሚደረግ ነገር አይኖርም ። እነዚህን ለሟሟላት ቢያንስ ወራትን ምናልባትም 3ወር 5ወር ሊፈጅ ይችላል። በመሃል የሚጎዱት ተማሪዎቹ ናቸው።
ወደ መፍትሄው ስመጣ ሁለት የመፍትሄ ሃሳቦች ይታዪኛል:

የመጀመሪያው ፦ ከሌሎች ክልል የመጡ ተማሪዎች በሃገራቸው ወይም በአቅራቢያቸው በሚገኙ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸው ካቋረጡበት እንዲጀምሩ
ሁለተኛው፦ በዛው አካባቢ ያሉ የአክሱምና የአዲግራት ተወላጅ ተማሪዎች ደግሞ በአንፃራዊነት መቀሌ ዩኒቨርስቲ ሰላም ስለሆነ እዛ እንዲማሩ መንግስት ቢፈቀድላቸው የተሻለ ነው።
እናንተም ለትምህርት ሚኒስቴርና ለ MOSHE ቅርብ የሆናቹ ባለሙያዎች የእነዚህ ሁለት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እጣፈንታ መንግስት በቅርብ ቀን በተቋማቱ በኩል መፍትሄ እንዲበጅለት የዘወትር ጉትጎታችሁ አይለየን።
አመሰግናለው
M ነኝ ከአዲስአበባ


#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT