🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የተማሪዎች መልዕክት ሰላም ኪራ! ስሜ ይቆየኝ እና የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ። እናም ዛሬ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

የተማሪዎች መልዕክት

ሰላም ኪራ!
ስሜ ይቆየኝ እና የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ። እናም ዛሬ ዩኒቨርሲቲያችን ጥሪ እንዳስተላለፈ የለጠፋችሁትን አየሁት፡፡ ነገር ግን ከደስታ ይልቅ ስጋት እና ፍትሃት ነው የተሰማኝ፡፡ ምክንያቱም አካባቢው ላይ ስላለው ነገር የሚወራው እና የምንሰማው ነገር ምንም ደኅንነት እንዲሰማን የሚያደርግ ነገር ስላልሆነ ነው።

እዛ ያሉ ጓደኞቻችን እንደሚነግሩን አሁንም ድረስ ችግር እንዳለ እና እንዳልተረጋጋ ነው። በዜና የምንሰማው እና እነሱ የሚነግሩን በጭራሽ አይገናኝም፡፡

እና ትምህርት ሚኒስቴርም በለው ወይም Moshe ከዚህ በፊት ስንል እንደነበረው በያለንበት ይመድቡን አልያም ራያ ዩኒቨርሲቲ እንደሰማነው እንዳይከሰት በቂ የሆነ ጥበቃ ያድርጉልን። ተመራቂ ተማሪዎች ሲመለሱ በመንገድ ያጋጠማቸውን በሰማንበት የኛም ደኅንነት ያሳስበናልና መጥራት ብቻ ሳይሆን ደህንነታችንን ማስጠበቅንም መንግስት ሊያስብበት ይገባል።


እናንተም መረጃ ስለምታደርሱን እና መልዕክቶቻችንን ሳትታክቱ ስለምትቀበሉን ድምጽም ስለምትሆኑን በግሌ ምስጋናዬ ወደር የለውም። እንወዳችኋለን።

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT