🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በመላው ኢትዮጵያ ተቋርጦ የነበረው የቴሌግራም አገልግሎት አሁን መስራት ጀምሯል! ኢትዮጵያ ቼክ | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

በመላው ኢትዮጵያ ተቋርጦ የነበረው የቴሌግራም አገልግሎት አሁን መስራት ጀምሯል!

ኢትዮጵያ ቼክ ማረጋገጥ እንደቻለው የቴሌግራም መተግበርያ በመላው ኢትዮጵያ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ መስራት አቁሞ ነበር።

በበርካቶች ዘንድ መልእክት ለመለዋወጫ ተመራጭ እየሆነ የመጣው ቴሌግራም ለምን መስራት እንዳቆመ በግልፅ ባይታወቅም ከ12ኛ ክፍል ፈተና ጋር ተያያዞ አንዳንድ የቴሌግራም ግሩፖች ላይ ህገወጥ ፅሁፎች ሲንሸራሸሩ እንደነበር ቅሬታዎች ሲቀርቡ ነበር።

ከሚመለከተው አካል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሙከራ እያረግን የነበረ ሲሆን መልስ ማግኘት አልቻልንም። ዛሬ ቀትር ላይ የ12ኛ ክፍል ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ ቴሌግራም ዳግም መስራት ጀምሯል።

Via Ethiopia check

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT