🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

198 የሚሆኑ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኤጀንሲው ያቀረበውን የመረጃ ስርዓት ተከትለው ለአገል | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

198 የሚሆኑ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኤጀንሲው ያቀረበውን የመረጃ ስርዓት ተከትለው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ለ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝግጅት ምን እንደሚመስል አሐዱ ያናገራቸው በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የእውቅና ፍቃድ አሰጣጥ ዳይሬክተር አቶ አብይ ደባይ ኤጀንሲው የመረጃ ስርዓትን በመዘርጋት ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኤጀንሲው ያዘጋጀውን የመረጃ ስርዓት ተከትለው ለመማር ማስተማር አገልግሎት ዝግጁ ናቸው ያሉት ዳይሬክተሩ ከ278 ተቋማት ውስጥ 198ቱ በመረጃ ስርዓቱ ውስጥ የገቡ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

2013 የትምህርት ዘመን ትምህርት ለመስጠት ዝግጁ የሆኑ ተቋማት በቅድሚያ ኤጀንሲው የዘረጋውን የመረጃ ስርዓት ተከትለው ለቁጥጥርና ክትትል የሚመች ማስረጃን ማቅረብ አለባቸው ያሉት አቶ አብይ ከዚህ ውጪ ያሉት ግን የእውቅና ፍቃድ አይሰጣቸውም ብለዋል፡፡ኤጀንሲው ይህንን መተግበር መቻሉ ከዚህ ቀደም በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የሚታየውን ህገ-ወጥ አካሄድ ለመቅረፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

[አሐዱ ራድዮ 94.3]

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT