🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ዩኒቨርሲቲዎች በ2013 የመጀመሪያ አመት መቀበል የሚችሉትን የተማሪ ቁጥር ለሳይንስ እና ከፍተኛ ት | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

ዩኒቨርሲቲዎች በ2013 የመጀመሪያ አመት መቀበል የሚችሉትን የተማሪ ቁጥር ለሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቃቸዉን ገለጹ፡፡

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የ2012 አ.ም የ12ኛ ክፍል ትምህርት በመቋረጡ አጠቃላይ ሀገራዊ ፈተና ባሳለፍነዉ ሳምንት መሰጠቱ ይታወቃል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴርም የፈተናዉን ዉጤት በአጭር ጊዜ እንደሚያወጣ አሳዉቋል፡፡ ሀገር አቀፍ የፈተና ዉጤት ይፋ ሲደረግ ከዚህ ቀደም ከነበረዉ መደበኛ የትምህርት መርሃግብር የተለየ ይሆናል፡፡

ዩንቨርስቲዎች ነባር ተማሪዎችን በቅርቡ ከመቀበላቸዉ አንጻር የመጀመሪያ አመት ተማሪዎችን ለመቀበል ምን ያህል ዝግጁ ናችሁ ሲል አሀዱ የተለያዩ ዩንቨርስቲዎችን ጠይቋል፡፡

የአዳማ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ለሚ ጉታ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የትምህርት መርሀ ግብሩን አዛብቶታል ብለዋል፡፡

ቢሆንም የ2013 አ.ም የመጀመሪያ አመት 2 ሺ 200 ተማሪዎችን ለመቀበል የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች አድርገን ለሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርም አሳዉቀናል ብለዋል፡፡

የ2013 አ.ም የመጀመሪያ አመት ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅታችንን አጠናቀን ለሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርም ከ4 ሺ 500 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ያስታወቁት ደግሞ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ታፈረ መላኩ ናቸው፡፡

በተመሳሳይ የወላይታ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ በሶስት ካምፓሶች 4ሺ የሚሆኑ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራን ነዉ ብለዋል፡፡

አሐዱ ቴቪ

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT